የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎችን በማጠናከር የወንጀል ምጣኔን መቀነስ ላይ በትኩረት እየተሰራበት ያለውን ሂደት በቀጣይ ቀናት ተጠናክሮ ይቀጥላል።
የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎችን በማጠናከር የወንጀል ምጣኔን መቀነስ ላይ በትኩረት እየተሰራበት ያለውን ሂደት በቀጣይ ቀናት ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ :- የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ክ/ከተሞች የቅድመ ወንጀል መከላከል ላይ ትኩረት በማድረግ ጨለማ ቦታዎችን በብርሀን እንዲሞሉ የውስጥ ለውስጥ መንገድ መብራት ማስበራት ፣ የደህንነት ካሜራ ገጠማ ስራን በብሎኮች ፣ በተቋማትና በት/ቤቶች ዙሪያ ትኩረት በማድረግ በቀጣይ የሚሰራ መሆኑን የከተማው የመብራት አስበሪ ፣ የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማና የሞዴል ፖሊስ ሴንተር ፈጠራ ኮሚቴ የመጀመሪያ ዙር አፈፃፀሙን በመገምገም የቀጣይ ዕቅዱን ተወያይቶ የቀጣይ አቅጣጫ ባስቀመጠበት ወቅት ገልጿል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲሰ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ሞዴል ብሎኮችን የመፍጠር ፣ ጨለማ ቦታዎችን በብርሀን እንዲሞሉ ማድረግ ፣ የሲሲቲቪ የደህንነት ካሜራ ገጠማ ስራዎችንና የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ ሴንተሮች በማዘመን የከተማውን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥና የነዋሪውን ደህንነት መጠበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራበት ያለውን አግባብ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም ህዝቡን በማሳተፍ መብራት የማስወጣት፣ የደህንነት ካሜራ በተለይም የንግድ ተቋማት እንዲገጥሙ ማድረግ፣ የወንጀል መከላከል ስራዎችን ማጠናከርና ህብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ የፀጥታና የደህንነት ስራዎችን በትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
አቶ ወልዴ ወገሴ የጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አሰፈፃሚ እንዳሉት በመደመር መንግስት በመጣው ለውጥ ቀዳሚ ተጠቃሚና ለመንግስት ገቢ የሚያስገኝ የገበያ መአከል የሚገኝበት ክ/ከተማ መሆኑን አንስተው በዚህም ህብረተሰቡ የሰላም ባለቤት በመሆን የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ በባለቤትነት እየሰሩ ያለውን አጠናክረው የሚያስቀጥሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ በኮሚቴው የተሰሩ ሰራዎችና በቀጣይ የተያዙ ዕቅዶችን ሲያቀርቡ እንዳሉት በመጀመሪያው ዙር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን አንስተው በቀጣይም ኮሚቴው የያዛቸውን ዋና ዋና ተግባራትን አብራርተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ የኮሚቴ አባላቱም ባለፉት ጊዚያት የነበሩ ጥንካሬዎችን ማጠናከርና አልቆ መፈፀም እንደሚገባ አንስተው ለዚህም ህብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ የፀጥታና የደህንነት ስራ የሚሰሪ መሆኑን ገልፀዋል።
ጥቅምት 19/2019ዓ.ም
ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79