የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አስበሪ ፣ የሲሲቲ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አስበሪ ፣ የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማና የሞዴል ፖሊስ ሴንተር ፈጠራ ኮሚቴ በጉለሌ ክ/ከተማ የትግበራ ሂደቱን የመስክ ምልከታ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አስበሪ ፣ የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማና የሞዴል ፖሊስ ሴንተር ፈጠራ ኮሚቴ በጉለሌ ክ/ከተማ የትግበራ ሂደቱን የመስክ ምልከታ አደረገ።

በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የተመራዉ የመብራት ማስበራት ግብረሃይል በክፍለ ከተማዉ ያሉ ወረዳዎችን የዉስጥ ለዉስጥና የመንገድ ዳር መብራቶች እንዲሁም የሲሲቲቪ ካሜራ ገጠማ ስራ ያሉበትን ሁኔታ የመስክ ቅኝት አካሄዷል።

ኮሚቴው በተለያዩ ዙሮች ከማእከል አስከ ወረዳ ያሉ አመራሮችን ባሳተፈ መልኩ በክፍለ ከተሞች በምሽት በመዘዋወር መብራት የማስበራት ስራ ሲሰራ የቆየ ሲሆን ፤ በዛሬዉ እለት በሁለተኛ ዙር በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመገኘት ከዚህ ቀደም በምሽት ለመንቀሳቀስ ስጋት የሆኑ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ብርሃናማ የሆኑ ስፍራዎችና ዘመናዊ የደህንነት ካሜራ ገጠማ ስራን ተዘዋውሮ የመስክ ምልከታ አድርጓል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ከተማውን የሚመጥን የሰላምና የደህንነት ስራዎች በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎችን ላይ የህብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ በመስራቱ የወንጀል ምጣኔን መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል።

ወ/ሮ ሊዲያ አክለውም ሞዴል የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ማዕከላትን በማዘመን የከተማችንን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ውጤታማ ስራዎች በመስራት የህዝቦችን በሰላም ወጥቶ መግባት ማረጋገጥ መቻሉንና ከተማዋ የሰላም ተምሳሌት ከተማነቷን ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ስራ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ወልዴ ወገሴ የጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በክ/ከተማው የሚገኙ ጨለማ ቦታዎችን በብርሀን መሙላት ፣ የደህንነት ካሜራ መግጠምና የፖሊስ ሴንተሮችን በማዘመን ከህብረተሰቡ ጋር በትብብር መስራቱን አንስተው በዚህም ሞዴል ብሎኮችን በመፍጠር ሰላሟ የተረጋገጠባትና የነዋሪዎቿ ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ብለው በዚህም በከፍተኛ መጠን የወንጀል ምጣኔን መቀነስ መቻሉን አብራርተዋል።

አቶ ተስፋዬ ፈይሳ የጉለሌ ክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ በክ/ከተማው ከዚህ ቀደም በተለይም በምሽት ለመንቀሳቀስ ስጋት የነበሩ ቦታዎችን በብርሀን እንዲሞሉ በማድረግና የደህንነት ካሜራ ገጠማ ስራዎች ህብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ መስራት መቻሉንና በዚህም ተጨባጭ ውጤት ማምጣት መቻሉን አብራርተዋል።

ጥቅምት 19/2019ዓ.ም

ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79