የሃይማኖት አባቶች ለብሔራዊ መግባባትና ለሰላም...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሃይማኖት አባቶች ለብሔራዊ መግባባትና ለሰላም ግንባታ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ።

የሃይማኖት አባቶች ለብሔራዊ መግባባትና ለሰላም ግንባታ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ "ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ" በሚል መሪ ቃል ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱም ወቅት፣አቶ ፍሰሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰለምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በበኩላቸው፣ ሀገራችን በልማትና በብልጽግና ተስፋ ላይ በምትገኝበት ወቅት፣ በሀገራዊና ብሔራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ልዩነቶችን በውይይት፣ በመደማመጥና በመግባባት መፍታት ይገባል ያሉት አቶ ፍሰሐ፣የሃይማኖት ተቋማትና የሃይማኖት አባቶች ትውልድን በሥነ-ምግባር፣ በሰላም እሴቶችና በሀገር ፍቅር የመቅረጽ ኃላፊነታቸውን በተጠናከረ መልኩ መወጣት እንዳለባቸው በማስገንዘብ በዚህም ብሔራዊ መግባባትን በማጠናከር ዘላቂ ሰላምንና የሀገር ግንባታን ለማረጋገጥ የጋራ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።

አቶ አዲስ ዘውዴ የአቃቂ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ እንደተናገሩት፣ የዛሬው “ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ለሀገር ግንባታ” በሚል ርዕስ የሚካሄድ መድረክ ሲሆን፣በሀገራችን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የአመለካከት ልዩነቶች ቢኖሩም፣ የሃይማኖት አባቶች በሰላም፣ በአንድነትና በመቻቻል ላይ በመስበክ ማህበረሰቡን የማስተሳሰርና ልዩነቶችን የማጥበብ ሚናቸውን በመወጣት የሀገራችን ሰላም እንዲጸናና የህዝቦች አንድነት እንዲጠናከር የሃይማኖት ተቋማትና የሃይማኖት አባቶች ኃላፊነት የጎላ መሆኑንም አመልክተዋል።

አቶ እንዳለ ፀጋዬ የኃይማኖት ጉዳዮችና የሰለም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ተወካይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፣ለውይይት የሚሆን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፣ በሰነዱም በሀገር ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት አካታችነትን፣ የሽምግልና ሥርዓትንና የውይይት ባህልን ማጠናከር ያለው ፋይዳ የዳሰሱ ሲሆን፣ በተጨማሪም በመንግሥትና በሃይማኖት ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት ሊያዳክሙ የሚችሉ ፈተናዎችን በመለየት፣ በመተማመን፣ በትብብርና በጋራ ኃላፊነት ላይ የተመሠረተ ግንኙነት መገንባት ለዘላቂ ሰላምና ለሀገር ግንባታ ያለው አስተዋፅኦ አብራርተዋል።

ጥቅምት 19/2019ዓ.ም

ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79