በወቅታዊ የፀጥታና የደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በግብይት ስርአት ላይ እየተስተዋሉ ባሉ አዝማሚያዎች ዙሪያ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ።
በወቅታዊ የፀጥታና የደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በግብይት ስርአት ላይ እየተስተዋሉ ባሉ አዝማሚያዎች ዙሪያ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ።
የከተማውን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥና የግብይት ስርአቱን መስመር ለማስያዝ ጥናትንና ጥልቅ ምርመራን መሰረት በማድረግ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገልጿል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የክትትል ሂደቱን ሲገመግሙ እንዳሉት በመረጃና ማስረጃ ላይ መሰረት በማድረግ አሰራርን በጠበቀ መልኩ የክትትል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው የንግድ ስርአቱን ህጋዊነትን ለማስጠበቅና የነዋሪውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል።
ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም የግብይት ስርአት ሰንሰለቱ በጥልቀት በመመርመር መፍትሄ የመስጠት የሚያስችል የህግ ማስከበርና አሰራርን የማስጠበቅ ስራ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡም አስፈላጊውን ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስበዋል።
ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም
ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79