መደበኛ የፀጥታ ሥራዎችን ከወቅታዊ ስራዎች ጋር በማጣጣምና በማቀናጀት መስራት በመቻሉ በከተማው ላይ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ማምጣት ተችሏል።
መደበኛ የፀጥታ ሥራዎችን ከወቅታዊ ስራዎች ጋር በማጣጣምና በማቀናጀት መስራት በመቻሉ በከተማው ላይ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ማምጣት ተችሏል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ :- የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በበጀት ዓመቱ የፀጥታ ፣ የደህንነት ፣ የወንጀል መከላከልና መሰል ተግባራትን በዕቅድ ይዞ እየሰራ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የ90 ቀን ልዮ ዕቅድ በማቀድ ወደ ስራ በገባው መሰረት አፈፃፀሙን ገምገሟል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት መደበኛ ስራዎችን ከወቅታዊና አሁናዊ ጉዳዮች ጋር አቀናጅቶ መምራትና በማከናወን ተጨባጭ ውጤት ማምጣት ተችሏል ብለዋል።
ሕዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የወንጀል ቅድመ መከላከል ሥራዎችን በማጠናከርና የሰላም ዕሴት ግንባታን በማጎልበት ሕብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ የፀጥታና የደህንነት ስራዎች እየተሰራና በዚህም ተጨባ ጭ ውጤት መመዝገቡን የገለፁት ቢሮ ኃላፊዋ በተመሳሳይ የወንዝ ዳርቻዎችን ማልማት፣ የፍሳሽ አወጋገድን ማሻሻል፣ የመንገድ ደህንነትን መጠበቅ ፣ የኢኮኖሚ አሻጥርን መቆጣጠርና የምሽት ንግድ አገልግሎቶች እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ በተገቢው ሁኔታ እንዲሰጡ ግንዛቤ የመፍጠር ተግባራት በትኩረት የተሰራበት አግባብ መኖሩን ገልፀዋል።
የቢሮው ዕቅድና በጀት ክትትል ድጋፍና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ ቢሮው በ90 ቀናት ከ15 ቀን ዕቅድ አፈጻጸምን ሪፖርት ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፣በገለጻቸውም የግምገማ መድረኩ የተከናወኑ ተግባራትን፣ የተመዘገቡ ውጤቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመገምገም ቀጣይ ሥራዎችን በተሻለ መልኩ ለማስፈጸም አቅጣጫ ለማስቀመጥ ውጤታማነትን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
በሪፖርቱም በተጀመሩት የ90 ቀናት ዕቅድ ውስጥ የተከናወኑ ሥራዎችን ከዕቅድ አንጻር በመፈተሽ፣ ያልተሳኩ ተግባራትን ለመለየትና ለማስተካከል፣ በቀጣዮቹ ቀናት መከናወን የሚገባቸው ሥራዎች አንስተው፣ቅንጅታዊ አሠራር በማጠናከር የተያዙ ዕቅዶችን በወቅቱና በውጤታማነት ለማስፈጸም እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።
በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
ጥቅምት 18/2019 ዓ.ም
ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79