የሃይማኖት አባቶች የሰላም አምባሳደሮች እንደመሆናቸው የሀገር ገፅታ ግንባታን ማረጋገጥ ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።
የሃይማኖት አባቶች የሰላም አምባሳደሮች እንደመሆናቸው የሀገር ገፅታ ግንባታን ማረጋገጥ ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት በሰላም እሴት ግንባታና በሀገር ግንባታ ዙሪያ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል። ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠልም በየካ ክ/ከተማ ከሚገኙ ከተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት መሪዎችና አባቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።
አቶ ፍሰሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ኃላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንዳሉት የሃይማኖት ተቋማት በመልካም ተግባራትና በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ ከሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በተጨማሪ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልጸው ፣ በዜጎች መካከል መከባበር ፣ በሥነ ምግባር የታነፀ ማህበረሰብ መፍጠር ፣ የእርስ በርስ ትስስርን ማጎልበት እንዲሁም የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን በሰላማዊ ውይይት መፍታትን ባህልን ያደረገ ዜጋ እንዲኖር የሀይማኖት ተቋማት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ።
የሃይማኖት ተቋማት ብሔራዊ መግባባትን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም እና ለሀገር ግንባታ ሚናቸው የጎላ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ህብረተሰቡ ልዩነቶችን እንደ ሀብት በመመልከት በመከባበርና በመተባበር የጋራ እሴትንና አንድነትን ማጠናከር ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ማስተማር እንደሚገባም ሀላፊው አሳስበዋል።
ሼህ አቡዱልሀሚድ አህመድ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ም/ል ፀሐፊ የመድረኩን አላማ ሲገልፁ እንዳሉት የሀገራችን ሰላምና ደኅንነት ዘላቂ እንዲሆን እንዲሁም የሰላም ዕሴቶቻችንንና ባህላችንን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ለማድረግ መሆኑን ጠቅሰው ፣ የሃይማኖት ተቋማት በማኅበረሰቡና በአካባቢያቸው የመግባባት፣ የመቻቻል፣ የሰላምና የፍቅር መልዕክቶችን በማስተማር የሰላም ባህልን በማሳደግና በማጠናከር ለማኅበረሰቡ ሰላማዊ አብሮነትና ለሀገራዊ ሰላም ዘላቂነት የላቀ ሚናቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ ሀብታሙ ደረጀ የየካ ክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት፣የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሰላም የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ለዘላቂ ሰላም እና ለሀገር ግንባታ የሚያበረክቱትን ሚና አይተኬ ነው ብለዋል።
"ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ" በሚል ርዕስ አቶ ኤሊያስ ቀጄላ የኃይማኖት ጉዳዮች ቡድን መሪ ለውይይት የሚሆን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፣በገለጻቸውም ብሔራዊ መግባባት ለማጠናከር የጋራ ችግሮችን በግልጽነት መወያየት፣ ልዩነቶችን በመከባበር መቀበልና የጋራ ተጠቃሚነትን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑንን ጠቁመዋል።
ግጭቶችን በውይይትና በሽምግልናና መፍታት፣ አለመግባባቶችን በእርቅ ማደስ ፣የሕዝብና የሃይማኖት ተቋማት ትብብርን ማጠናከር ፣ እንዲሁም የሰላማዊ ውይይት ባህልን ማዳበር ለትውልድ ግንባታና ለሀገራዊ አንድነት መሠረት እንደሚሆኑ አቶ ኤሊያስ አብራርተዋል።
ጥቅምት 18/2019ዓ.ም
ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79