"ብራንድ ማንነታችን፣ ውጤት መለያችን!”

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

"ብራንድ ማንነታችን፣ ውጤት መለያችን!”

"ብራንድ ማንነታችን፣ ውጤት መለያችን!”

በተቋም ግንባታና በብራንዲንግ ማንዋል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ አመራሮችና አስተባባሪዎች “ብራንድ ማንነታችን፣ ውጤት መለያችን!” በሚል መሪ ቃል በተቋም ግንባታ ብራንዲንግ ማንዋልን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት አቶ ጌታሁን አበራ የቢሮ ዋና አማካሪ ተቋሙን የሚገልጸው ብራንድ ምንነት በተመለከተ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠርና መድረኩ መዘጋጀቱን ገልፀው የተቋም ግንባታን የሚያጠናክሩ መሠረታዊ ጉዳዮችን መገንዘብና ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ተቋሙን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ብቁና ዘመናዊ ክህሎት ያላቸውን ሙያተኞች ማፍራት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመንና የሪፎርም ሥራዎችን በተጠናከረ መልኩ መተግበር የተቋም ግንባታን ከማጠናከር አንጻር ወሳኝ መሆናቸውንም ሀላፊው አመልክተዋል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍሰሐ ጥበቡ በበኩላቸው፣

ብራንዲንግ የተቋሙን አጠቃላይ ሥራ፣ ማንነት፣ ስልታዊና ራዕያዊ እሴቶች እንዲሁም ለሕዝብ የሚተላለፉ መልዕክቶችን በግልጽና በተቀናጀ መልኩ የሚያሳይ ሂደት መሆኑን አብራርተዋል።

በተጨማሪም የተቋሙ አርማ ፅንሰ-ሐሳብና ትርጉም፣ የቀለም ምርጫ፣ የመገናኛ እና የመልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች የተቋሙን ማንነት በመግለጽና በሕብረተሰቡ ዘንድ ተገቢ ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

አቶ ፍሰሐ አክለውም፣ ለሰላምና ፀጥታ ተቋም የሚመጥን ብራንዲንግ እምነትን፣ ደህንነትን፣ ታማኝነትንና ሙያዊ ብቃትን ማንጸባረቅ እንዳለበት ጠቁመው፣እነዚህ እሴቶች የተቋሙን ሙያዊ ማንነት በማጠናከር በሕዝብ ዘንድ እምነትና ተቀባይነት ለማሳደግ ወሳኝ መሆናቸውንም አስረድተዋል።

በአጠቃላይ የብራንዲንግ ማንዋሉ በተቋሙ የሚገኙ አካላት የጋራ ማንነትና የሥራ ባህል እንዲኖራቸው፣ የተቋሙ መልዕክት በተቀናጀ መልኩ እንዲተላለፍና የተቋም ግንባታ ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጠቁመዋል።

ጥቅምት 14/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79