ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ !!

ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ !!

ሀገር በፈተናዎች ስታልፍ የእምነት ተቋማት የድርሻቸውን አብረው በመፈተን ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ከፍ እንድትን ሀላፊነታቸውን በሚገባ ተወተዋል።

አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ

ልዩነቶችን በአንድነት ውስጥ በመቀበል፣ ችግሮችን በውይይት መፍታትና የጋራ ሀገራዊ እሴቶችን በማጠናከር የተረጋጋች ሀገርን አጽንቶ ለማቆየት እንዲሁም የጋራ የሆነ ሀገርን ለመገንባት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ "ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ" በሚል መሪ ቃል ከሀይማኖት ተቋማት አባቶችና መሪዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል በዛሬው ዕለትም በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከሚገኙ የሀይማኖት መሪዎችና አባቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።

አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ እንዳሉት ልዩነቶችን እንደ ውበት በመውሰድ ለሀገር ሁለተናዊ ዕድገት ተቀራርቦ በመስራት ብሔራዊ መግባባትና ማህበራዊ ትስስር መገንባት እንደሚገባ ገልፀዋል ።

የሀይማኖት ተቋማት በብዝሀነት የጋራ እሴቶች ማጎልበት ላይ ትኩረት ማድረግ ፣ ልዩነቶችን በንግግር መፍታት የሚችል ዜጋ በመፍጠርና የሰላም እሴትን መገንባት ላይ የሀይማኖት ተቋማት እየሰሩት ያለውን ስራ አጠናክረው ማስቀጠል እኔደሚገባ አቶ ብርሀኑ ተናግረዋል።

ብሔራዊ መግባባትን መሰረት በማድረግ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሀይማኖት ተቋማት ወሳኝ ሚና እንዳላቸውና በልዩነቶች ውስጥ አብሮነትን በማጠናከር ከሌሎች ሀገራት ቀዳሚ የሰላም ተምሳሌት ሀገር ባለቤት መሆኗን ማስመስከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ አህመድ ሀሰን የንፍስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው ህዝቦች በእምነት እሳቤና ድንጋጊ ውስጥ ተከባብረው ፣ ተዋደውና ታንጸው እንዲኖሩ ለሀይማኖታቸው ተገዥ እንዲሆኑ በማስቻል ሀገራችንን ለዘመናት የአብሮነት ሀገር እንድትሆን በዜጎች የአብሮነት ካስማ በጋራ ትብብር የቆመች ሀገርን በማስቀጠል ለተተኪው ትውልድ በማስተላለፍ አብሮነትንና ኢትዩጵያዊ የሆኑ እሴቶችን ማጎልበት ከሁሉም ቤተ እምነቶችና የሀይማኖት ተቋማት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።

ሼህ አብዱል ሀሚድ አህመድ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ም/ዋና ጸሀፊ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፍት መልዕክት በሰላምና በጋራ እሴት ግንባታ ላይ የጋራ ሀላፊነትን በመውሰድ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታትና ሰላምን በመስክ እሴቶቻችንን በማጠናከር ሀገር ግንባታ ላይ ትልቆ ኃላፊነትና ድርሻ እንዳላቸው በመገንዘብ መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል።

አቶ እንዳለ ጸጋዬ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የይማኖት ጉዳዮች ተወካይ ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ በሚል ጉዳይ ላይ ለውይይት የሚሆን ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ከሀይማኖት አባቶቹ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ምላሽ ተሰቶበታል።

በቀጣይ ቀናትም በሌሎች ክ/ከተማች ላይ ውይይቱ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል።

ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79