የስጋ ዋጋ ጭማሪ በሚስተካከልበት ሁኔታ ከስጋ ቤት ባለቤቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።
የስጋ ዋጋ ጭማሪ በሚስተካከልበት ሁኔታ ከስጋ ቤት ባለቤቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።
ጥቅምት 11/2019 ዓ ም
የስጋ ቤት ባለቤቶች ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮና ከሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ጋር ባደረጉት ውይይት በማህበራቸው አማካይነት ተወያይተው የዋጋ ማስተካከያ እንዲያደርጉ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
መድረኩን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅና የአዲስ አበባ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በጋራ መርተውታል።
ከመድረክ የስጋ ቤቶች የዋጋ ጭማሪ አንፃር የተካሄደ ዳሰሳ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች ከእርድ ከብት ጋር ተያይዞ በግብይት ሂደት የሚታዩ የደላላ ጣልቃ ገብነት ችግርን በማንሳት መንግስት እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል።
ከእርድ ከብት አቅርቦት አንፃር ችግር ሳይኖር ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ሊኖር አይገባም ያሉት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የስጋ ዋጋ የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ታሳቢ ያደረገ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አያይዘው የከተማ አስተዳደሩ በከተማችን በሚገኙ አምስት የቁም ከብት የገበያ ማዕከላት ላይ አርሶአደሩ ምርቱን በቀጥታ ይዞ እንዲቀርብ በማድረግ የስጋ ቤቶች የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
በመድረኩ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት በስጋ ዙሪያ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት በዘርፉ እሴት የማይጨምሩ ህገ-ወጥ ደላላዎችን ከገበያው የማስወጣትና ሌሎች የቁጥጥር ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ይሰራል ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ አያይዘውም በቀጣይ ከግብር፣ ከንግድ ፍቃድ አንፃር የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው የልኳንዳ ማህበራት ተወያይተው አሁን ያለውን ንረት ታሳቢ ያደረገ የዋጋ ተመን እንዲያወጡ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የስጋ ቤት ባለቤቶች በማህበራቸው አማካኝነት ተወያይተው በአጭር ጊዜ የዋጋ ማስተካከያ አድርገው እንዲያሳውቁ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ
https://linktr.eተተተተe/qr/e5702bda-a953-4926-8253-