ቢሮው አምስት ቴክኖሎጂዎችን በማልማት ወደ ስራ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ቢሮው አምስት ቴክኖሎጂዎችን በማልማት ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ።

ቢሮው አምስት ቴክኖሎጂዎችን በማልማት ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ።

የከተማውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥና አገልግሎቶችን  በቴክኖሎጂ  ለመስጠት ቴክኖሎጂን  በማልማት ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገልፀ።

ቢሮው  ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች  ውስጥ አምስት አገልግሎቶችን   በቴክኖሎጂ   ለመሰጠት  ከአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ  ቢሮ ጋር በመተባበር   ያለማ  ሲሆን አገልግሎቶቹም የተቋም ደህንነት መከታተያ ፣ የሰላም ሰራዊት መረጃ ማረጋገጫ  ፣ የሀይማኖት ተቋማት ቅሬታ መቀበያ ፣ የፀጥታ መረጃ መቀበያ  እና የኩነት ፈቃድ ማመልከቻና መቀበያ እንደሆኑ የሁለቱ ተቋማት የማኔጅመንት አካላትና የሲስተም ባለሙያዎች ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት አስታውቋል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት በቢሮው አሁን ያለማቸውን  ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ አስራ ሁለት ቴክኖሎጃዎችን በማልማት ወደ ስራ መግባቱን አንስተው በዚህም የከተማውን ሰላም  በዘላቂነት ለማረጋገጥና የህብረተሰቡን  የአገልግሎት ተጠቃሚነት በማሳደግ  ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።

ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም በቢሮው ከለማው ቴክኖሎጂ መካከል የፀጥታ መረጃ መከታተያና የሁኔታ መከታተያ በተለይም የከተማውን የደህንነት ሁኔታ በአንድ መአከል ክትትል የሚደረግበት መሆኑንና በተለያዩ መንገዶች የሚገኙ ካሜራዎች  የምስልና የቪዲዮ መረጃን በመቀበል የቅድመ መከላከል ስራዎችን ለመስራትና የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ አቅም የሚሆን መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ አወሌ መሀመድ የአዲስ አበባ ከተማ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ  እንዳሉት የለሙት  ቴክኖሎጂዎች ለማንኛውም ተገልጋይ በእኩል ፣ በቅልጥፍናና በፍትሀዊነት መሰጠት የሚያስችል መሆኑን ገልፀው እነዚህን ቴክኖሎጂዎች በአግባቡ መጠቀም አንደሚገባና  እንደ ቢሮ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በቢሮው የለሙ ቴክኖሎጂዎችን ተዘዋውረው ምልከታ አድርገዋል።

ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም

ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ

https://linktr.eተተተተe/qr/e5702bda-a953-4926-8253-