ቅንጅታዊ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የከተማውን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
ቅንጅታዊ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የከተማውን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም ባለቤት ህዝብን በማድረግ በሰላም ሰራዊት በማደራጀት የፀጥታና የደህንነት ፣ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
ቢሮው ይህን አደረጃጀት ለማጠናከርና ውጤታማነቱን ለማስቀጠል ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣት ክንፍና ከአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት የጋራ ዕቅድ አቅደው በዕቅዱ ላይ ውይይት በማድረግ ወደ ስራ ገብተዋል።
አቶ አሰግድ ኃ/ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት የሰላም ሰራዊቱ ላይ የወጣቶችን ቁጥር ለመጨመርና የሰላምና ደህንነት ስራን ለማጠናከር የተያዘውን የቅንጅታዊ ስራን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበው ሁሉም ወደ ተግባር በመግባት የመረጃ ልውውጦችን በማዘመንና የጠራ መረጃ በመለዋወጥ ለከተማችን ሰላምና ሁለንተናዊ ዕድገት በጋራ በመስራት ለውጤት መትጋት ይጠበቃል ብለዋል።
አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ቢሮው ህዝብን የሰላም ባለቤት በማድረግ በከተማው ከሁለት መቶ ሺህ በላይ የሰላም ሰራዊት በማደራጀት የከተማውን ሰላም በማስጠበቅ ውጤታማ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
አቶ ፍስሀ አክለውም ይህን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል ዛሬ የተጀመረው ቅንጅታዊ ስራ በሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ላይ የወጣቱን ቁጥር ከፍ በማድረግ ሰላሟ የተረጋገጠባት ህዝቦቿ በሰላም ወጥተው መግባት እንዲችሉና እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን በውጤታማነት ተጠናቀው ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ወጣቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሰላም ከቤት ይጀምራል ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች ወጣቱ ለሀገር ብሎም ለከተማው ሰላምና ደህንነት ጉልህ ድርሻ እንዳለው ጠቁመው የዛሬው የቅንጅታዊ ስራ ወጣቱን ያሳተፈ የፀጥታና የደህንነት ስራዎችን መስራትና ለሀገሩ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆን የተጀመረው ቅንጅት ውጤት የሚያመጣና የከተማውን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ አቅም እንደሚሆን ገልፀው ወጣቱን የማስተባበርና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እንደሚሰሩ አብራርተዋል።
ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም
ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ
https://linktr.eተተተተe/qr/e5702bda-a953-4926-8253-