"ሀገር የሚገነባው በሰላምና በትውልድ ግንባታ ነ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

"ሀገር የሚገነባው በሰላምና በትውልድ ግንባታ ነው"

"ሀገር የሚገነባው በሰላምና በትውልድ ግንባታ ነው" 

  አቶ ብርሃኑ ረታ:-  የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና    ፀጥታ አስተዳደር ም/ቢሮ ኃላፊና የሃይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ

"ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ለሀገር ግንባታ " በሚል ርዕስ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በለሚኩራ  ክ/ከተማ ከተለያዩ   የሀይማኖት ተቋማት ከተውጣጡ የሀይማኖት መሪዎችና አባቶች ጋር ውይይት አደረገ።

አቶ ብርሃኑ ረታ  የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና  የሀይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት   ለዘላቂ ሀገር ግንባታ የሀይማኖት ተቋማት ሚና  ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው  እንደ ሀገር ብሎም እንደ ከተማ እየተሰሩ   የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ውጤታነት የሚረጋገጠው   ህዝቦቿ አንድነታቸውን በማጠናከር ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ብሔራዊ መግባባቶችን በማስቀጠል መሆኑን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ የብዝሀ ሀይማኖት ፣ እሴትና ቋንቋ ባለቤት እንደመሆኗ ህዝቦቿ እርስ በርስ በመደጋገፍና በመረዳዳት የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ   የወደፊት  እንድትቀጥል  የሃይማኖት ተቋማት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው  የእምነት ተቋማት በአስተምሯቸው የሰላምን ዋጋና የጋራ እሴቶችን ማስቀጠል ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ሊሰሩ እንደሚገባ  ገልፀዋል። 

ሼህ አብዱልሀሚድ አህመድ  የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ም/ል ዋና ጸሐፊ በመልዕክታቸው ሰላም የአንድ ሃይማኖት ብቻ ጉዳይ ሳይሆን የሁሉም የጋራ እሴትና የሀገር ግንባታ መሠረት መሆኑን ገልጸው  በእምነት የተለያየን ብንሆንም በሰላም፣ በመተሳሰብና በብሔራዊ መግባባት አንድ በመሆን ፣ በመቻቻልና በሕዝቦች መካከል የጋራ መግባባትን በማጠናከር  የሀይማኖት ተቋማት ሚና አይተኬ መሆኑን አመልክተዋል። 

የሃይማኖት አባቶችና ተቋማት የሰላም እሴቶችን በማስረጽ፣ የብሔራዊ አንድነትን በማጠናከርና ለሀገር ልማት የሚያግዝ የጋራ አመለካከት በመፍጠር የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ  ምክትል ፀሀፊው  አክለው አሳስበዋል።

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት  ኃላፊ አቶ አየለ ተስፋዬ   በመስከረም ወር የተከበሩ ሃይማኖታዊና ህዝባዊ  የአደባባይ በዓላት በሰላምና በመቻቻል እንዲከናወኑ የሃይማኖት አባቶች ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው እንደዚህ አይነት ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። 

አክለውም ሃላፊው ልዩነቶችን በአንድነት ውስጥ በመቀበል፣ አለመግባባቶችን በውይይትና በምክክር በመፍታት እንዲሁም የጋራ ሀገራዊ እሴቶችን በማጠናከር የተረጋጋችና ሰላሟ የጸና ሀገር ለመገንባት የሁሉም ዜጎችና የሃይማኖት ተቋማት የጋራ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ለሀገር ግንባታ በሚል ርዕስ አቶ ኤሊያስ ቀጄላ የሃይማኖት ጉዳዮችና፣የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ቡድን መሪ ለውይይት የሚሆን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፣በገለጻቸውም ሰላምን ለማስፈንና የሀገር ግንባታን በጋራ ለማስኬድ በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ጉዳዮች አቅርበዋል። 

በሰነዱም በሀገር ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት አካታችነትን፣ የሽምግልና ሥርዓትንና የውይይት ባህልን ማጠናከር ያለው ፋይዳ የዳሰሱ ሲሆን፣ በተጨማሪም በመንግሥትና በሃይማኖት ተቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት ሊያዳክሙ የሚችሉ ፈተናዎችን በመለየት፣ በመተማመን፣ በትብብርና በጋራ ኃላፊነት ላይ የተመሠረተ ግንኙነት መገንባት ለዘላቂ ሰላምና ለሀገር ግንባታ ያለው አስተዋፅኦ አጽንዖት ተሰጥቶታል።

ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም

ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ

https://linktr.eተተተተe/qr/e5702bda-a953-4926-8253-