የሰላም የጸጥታና የደህንት ስራዎችን በቅንጅት መስራት በመቻሉ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል።
የሰላም የጸጥታና የደህንት ስራዎችን በቅንጅት መስራት በመቻሉ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል።
አቶ ጌታሁን አበራ:- የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ
ግልፅ የሆነ የአሰራር ስርአትን በመዘርጋትና ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀሙን ከመአከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የቢሮው ሰራተኞች ጋር በገመገመበት ወቅት አስታውቋል።
አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ በውይይቱ ላይ እንዳሉት አጠቃላይ አመራሩ ፈጻሚ አካላትና ባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት በከተማው ላይ በሰላም በጸጥታና በደህንነት ዙሪያ በተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀው ትላልቅ የአደባባይ በዓላት እንዲሁም የመንግስት ምስረታን ጨምሮ በሩብ ዓመቱ በሰላም የተጠናቀቁበት እንደነበር ተናግረዋል።
የቢሮውን ተግባራት በመረዳት የመልካም አስተዳደር ስራ እንዲጠናከሩ ከማድረግ አንጻር ከሰላም እሴት ፣ ከአደረጃጀት ፣ ከጸጥታና መረጃ እንዲሁም ከኦፕሬሽን ዘርፍ አንጻር በአመለካከትና በአስተሳሰብ የዳበረ የበለጸገ በህግ ማስከበር አኳያም በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ አቶ ጌታሁን ገልጸው የሰላም የጸጥታና የደህንነት ስራዎች ሲከናወኑ በምቹ ሁኔታ ውስጥ ሳይሆን በርካታ ችግሮችን በማለፍና በብርታት መሆኑን ጭምር ጠቅሰዋል።
ሀላፊው አያይዘውም የመጣውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል የጠላት ሀይሎችን ሴራ ከጅምሩ ለማስቆም እንዲሁን ቀደሙ በብርታትና በትጋት በመስራት የከተማው ሰላም ከማስጠበቅ አንጻር ሀላፊነትን ለመወጣት በሙሉ አቅም መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
አቶ ማስረሻ ሀብቴ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በተያዘው በጀት ዓመት የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን የቢሮውን የሥራ እንቅስቃሴ የተከናወኑ ተግባራትን የተገኙ ውጤቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ቢሮው ትኩረቱ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ የከተማውን ሰላም በዘላቂነት በማረጋገጥ የህግ የበላይነትን ማስፈን ላይ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ በቀጣይም ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አብራርተዋል።
ከሰራተኞቹ ለተነሳሳው ሀሳብና አስተያየት ከመድረክ ምላሽ ተሰቶበት ውይይቱ ተጠናቋል ።
ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም
ዘላቂ ሰላም፣ አስተማማኝ ደህንነት ለተምሳሌት ከተማ!!!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ
https://linktr.eተተተተe/qr/e5702bda-a953-4926-8253-