ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ !!

ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ !!

ሀገር እንደ ሀገር እንድትቀጥል በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የሀይማኖት አባቶች ያላቸው ሚናና አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።

አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ

ልዩነቶችን በአንድነት ውስጥ በመቀበል፣ ችግሮችን በውይይት መፍታትና የጋራ ሀገራዊ እሴቶችን በማጠናከር የተረጋጋች ሀገርን አጽንቶ ለማቆየት እንዲሁም የጋራ የሆነ ሀገርን ለመገንባት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ "ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ" በሚል መሪ ቃል ከሀይማኖት ተቋማት አባቶችና መሪዎች ጋር ከአምስት ክ/ከተሞች ከተውጣጡ የሀይማኖት መሪዎችና አባቶች ጋር ውይይት አካሂዷል።

አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ እንዳሉት ለእርስ በርስ መግባባትና ለሀገር ግንባታ የሀይማኖት ተቋማት ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

ኃለፊው አክለውም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የትላንት ማንነቷን ለማስቀጠልና ነገዋን ለመገንባት የሀይማኖት ተቋማትና ቤተ እምነቶች አስተዋፅኦቸው ከፍተኛ መሆኑን አንስተው ሀገር ወዳድና እሴቱን የሚጠበቅ ትውልድ በመፍጠር የሀይማኖት አባቶች ሚናቸው አይተኬ መሆኑን በመገንዘብ በአስተምሮታቸው ላይ በማካተት በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ ሚናቸውን ማላቅ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

ኢትዮጲያ የብዝሀ ሀይማኖት ፣ እሴት ፣ ቋንቋና ባህል ያላት ሀገር እንደመሆኗ የእኩልነት ስርዓቱ እንዲሰፍን ብዙ ዋጋ የተከፈለላት ህዝቦቿ በጋራ ተጋምደው የሚኖሩባት መሆኗን ያነሱት የዘርፉ ኃላፊ ይህንንም በመደመር መንግስት ማጽናት ችለናልም ሲሉ የተደመጡ ሲሆን በይቅርታ የሽግግር ፍትህ ስንገነባ ልዩነቶቻችንን ትተን አንድነትን በማጠናከር በዘመናችን ዳግም ኢትዮጵያን ለማደፍረስ የሚጥሩ ሀይሎችን በመታገል አንድነታችንን በማፅናት ለዜጎቿ የምትመች ሀገር መገንባት ይጠበቃል ብለዋል።

ሼህ አብዱል አሚድ አህመድ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ም/ዋና ጸሀፊ በመድረኩ ተገኝተው እንዳሉት ሰላም የሚጸናው በዜጎች መካከል አብሮነትና መግባባት ሲኖር ልዩነቶችን እንደ ጌጥ በመቁጠር አመለካከቶችን በመልካም እይታ በመቀየር የጋራ ሰላም መገንባት፣ ለግጭት ሳይሆን ለሰላም በጋራ መቆም እንደሚገባ ገልጸው የሀይማኖት አባቶች በማህበረሰብ ውስጥ እሴትን በመገንባት በፍቅር ፣ በይቅርታ፣ በፍትህ በመኖር ከተግባር ጋር ተያይዞ ጠንካራ ህዝብ መገንባት እንደተቻለም ገልጸዋል።

አቶ እንዳለ ጸጋዬ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የይማኖት ጉዳዮች ተወካይ ብሔራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሀገር ግንባታ በሚል ጉዳይ ላይ ለውይይት የሚሆን ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ከሀይማኖት አባቶቹ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ምላሽ ተሰቶበታል።

ጥቅምት 6/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ

https://linktr.eተተተተe/qr/e5702bda-a953-4926-8253