"ስፖርታዊ ውድድሮች ለጋራ መግባባትና ለሀገር ግንባታ "
"ስፖርታዊ ውድድሮች ለጋራ መግባባትና ለሀገር ግንባታ "
በከተማችን አዲስ አበባ በርካታ ሁነቶች ያለፀጥታ ስጋት አብሮነትን ባጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜም የኢትዮጲያ ቡና ክለብና የቅዱስ ጊዎርጊስ ክለብ የእግር ኳስ ጨዋታ ያካሂዳሉ።
ጨዋታው ፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲከናወን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከከተማው ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር ከስፖርቱ ቤተሰብ ወጣቶች ጋር ውይይት አካሂደዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ስፖርታዊ ጨዋታቸው የእርስ በርስ ግንኙነት ባጠናከረና የሀገርን ገፅታ በሚገነባ መልኩ ማከናወን እንደሚገባ ገልፀው የክለቦቹ ደጋፊዎች ስፖርታዊ ውድድሮቹ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆኑና ስፖርታዊ ጨዋነትን ባነገበ መልኩ ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን የሚያጠናክሩ ሁነው እንዲከናወኑ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም ስፖርታዊ ጨዋታዎች ለመዝናኛና ለሀገር ግንባታ መጠቀምና የእርስ በርስ ግንኙነት ባጠናከረ መልኩ እንዲሆን የክለብ ደጋፊዎች ፣ አስጨፋሪዎችና ተቆጣጣሪዎች ኃላፊነት እንዳለባቸው አውቀው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና ከፀጥታ አካሉ ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
አቶ ዳዊት ትርፉ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ስፖርታዊ ውድድሮች ስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ ማከናወንና የስፖርቱን ኢንዱስትሪ ከፍ ባደረገ መሆን እንደሚገባ ገልፀዋል።
ም/ቢሮ ኃላፊው አክለውም በተለይም ውድድር በሚያደርጉ ክለቦች ተጨዋቾችና ደጋፊዎች መካከል የፀብ አጫሪ የሆኑ መልዕክቶችን ከማስተላለፍ መቆጠብ ፣ ስፖርትን ለአንድነትና የእርስ በርስ ግንኙነትን የሚያጠናክር እንዲሆን ማድረግ እንደሚጠበቅና ጨዋታዎቹ ተናፋቂ እንዲሆኑ ማድረግ የሁሉም የስፖርቱ ቤተሰብ ኃላፊነት መሆኑን ገልፀዋል።
ጥቅምት 6/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ
https://linktr.eተተተተe/qr/e5702bda-a953-4926-8253