የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና የመልካም አስተዳደር ክላስተር ቋሚ ኮሚቴ የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ ሪፖርት ገምግሞ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀመጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና የመልካም አስተዳደር ክላስተር ቋሚ ኮሚቴ የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ ሪፖርት ገምግሞ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀመጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና የመልካም አስተዳደር ክላስተር ቋሚ ኮሚቴ ዋና ተግባር በከተማው ላይ የሕግ ማስከበር ሥራዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ የሕግ ተፈጻሚነትን ማጠናከር እና ለሕዝብ ደህንነትና ሰላም የሚያግዙ ተግባራትን መከታተል ዋናው ተግባር ሲሆን የኮሚቴው ዋና ዓላማ በከተማዋ ሕግና ደንብ በአግባቡ መፈጸማቸውን በመከታተል ተጠያቂነትን በማጠናከርና የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሰላማዊና ደህንነቱ የተጠበቀና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች ከተማ መንባት ነው።
በዚህ መሰረት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊና የመልካም አስተዳደርና የህግ ማስከበር ቋሚ ኮሚቴ ዋና ሰብሳብ የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ ሪፖርቱን ገምግመው የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል በዚህም፡-
* የሰላም እሴትን በማጠናከር ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የወንጀል ምጣኔ እንዲቀንስ በማስቻል ህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት የከተማውን ሰላም አጽንቶ ማስቀጠል
*ዘመናዊ የሆነ የንግድ ስርዓት በማዘመን የዜጎች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
*የዜጎች ደህንነት ላይ ትኩረት በማድረግ ህጋዊ የሆነ የትራንስፖርት ፍሰት በማሳለጥ ከታሪፊ በላይ የሚያስከፉሉ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላትን በመቆጣጠር ህብረተሰቡን ከእንግልት በመታደግ ተጠቃሚ እንዲሆንና አካባቢን ከጸጥታ ስጋት የነጻ ማድረግ
*የትራፊክ ፍሰትንና የደንብ መተላለፉን ላይ ቁጥጥር ማድረግ
*የመንግስትና የህዝብን ጥቅም በማስፈን የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በትኩረት መስራት
*የደንብ መተላለፍ ላይ ትኩረት ያለው ስራ በመስራት የመከላከል የመቆጣጠርና የመሰረተ ልማቶች ስርቆት እንዳይፈፀም የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን መስራትና የወንዝ ዳርቻዎችን ከብክነት መቆጣጠርና መከላከል
* የአገልግሎት ጊዚያቸው ያለፈባቸውን ምግብና ምግብ ነክ የሆኑ ምርቶች በመቆጣጠር የዜጎችን ደህንነት መበጠቅ ጉዳቱን የሚፈጽሙ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ
*የተቀናጀ ፈጣን የአደጋ ስጋት መከላከል ስራዎችን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመስጠት አደጋ ስጋት ቅነሳ ላይ በትኩረት መስራት
* የጸረ ሙስና ትግሉን በማጠናከር ለብልሹ አሰራር ተጋላጭ የሆኑ ጉዳዩችን ቀድሞ ጥናት በማድረግ ተጠያቂነትን ማስፈን የሚሉት ይገኙበታል።
ጥቅምት 5/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ
https://linktr.eተተተተe/qr/e5702bda-a953-4926-825