"የከተማችንን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ፣ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥና ሕግና ደንብን የሚያከብር ማኅበረሰብ በመገንባት የተረጋጋች፣ለነዋሪዎቿ ምቹና ደህንነቷ የተጠበቀ ከተማ መፍጠር ተችሏል"።
"የከተማችንን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ፣ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥና ሕግና ደንብን የሚያከብር ማኅበረሰብ በመገንባት የተረጋጋች፣ለነዋሪዎቿ ምቹና ደህንነቷ የተጠበቀ ከተማ መፍጠር ተችሏል"።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ
ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
የአዲስ አበባ ከተማ የመልካም አስተዳደርና የህግ ማስከበር ክላስተር በ2019 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በክላስተሩ የተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት ማምጣት መቻሉን ከክላስተሩ አባላት ጋር አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት አስታውቋል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የክላስተሩ ሰብሳቢ እንደገለፁት በመደመር መንግሥት አስተሳሰብና በተቀናጀ የሥራ አካሄድ በመከተል ፣ የተቋማትንና የሕዝብን ተሳትፎ በማጠናከር ሰላም የሁሉም የጋራ ኃላፊነት መሆኑን በመውሰድ ፣ ባለፉት የሥራ ወቅቶች በሕግ ማስከበርና በፀጥታ ማስጠበቅ ረገድ በተከናወኑ የቅንጅት ሥራዎች የከተማውን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
በተለይም ከተማችን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችንና ከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ ያላቸውን ዝግጅቶች በሰላማዊና የተረጋጋ ሁኔታ ማካሄድ መቻሏ ፤ የተቀናጀ የፀጥታ ሥራ ፣ የሕግ ማስከበርና የሕዝብ ተሳትፎ ውጤት መሆኑን ጠቁመው ይህ ውጤት ሊጠናከር የሚችለው በተገኙ ውጤቶች ሳንዘናጋ ፣ ያሉ ክፍተቶችን በመለየትና የሥራ አፈጻጸማችንን በቀጣይነት በማሻሻል መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ኃላፊዋ ገልፀዋል።
ሀላፊዋ አክለውም የከተማችን የፍትሕ ሥርዓት እንዲጠናከርና ሕግን የሚያከብር ማኅበረሰብ እንዲገነባ ከፀጥታ ጉዳዮች ባሻገር በየዘርፉ የሚስተዋሉ የሕግና የደንብ ጥሰቶችን በመከላከል ፣ በትራንስፖርት ተርሚናሎች የትራፊክ መጨናነቅን መቀነስ፣ ሕብረተሰቡ ለእንግልት እንዳይጋለጥ ለማድረግ፣ የምግብና መድኃኒት ደህንነትን ማረጋገጥ፣ ጊዜው ያለፈባቸውና ለጤና ጠንቅ ሊሆኑ የሚችሉ ምርቶችን መቆጣጠር፣ እንዲሁም የቅዳሜና እሁድ ገበያን በማስፋትና የንግድ ፈቃድ የሌላቸውን ነጋዴዎች በሕግ ለመቆጣጠር የተከናወኑ ሥራዎች ለሕግ የበላይነትና ለማኅበረሰቡ ደህንነት መጠናከር ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው ገልፀው በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ አመላክተዋል።
በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ተሰጥቷል።
ጥቅምት 5/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79