የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከመደበኛ ስራዎቹ በተጨማሪ በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከመደበኛ ስራዎቹ በተጨማሪ በርካታ ሰው ተኮር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

ቢሮው በቀጣይ የ90 ቀናት ዕቅድ የከተማዋን የፀጥታና የደህንነት ስራዎችን የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የንቅናቄ ሰው ተኮርና መደበኛ ስራዎች ማስፈጸሚያ ዕቅድ ላይ ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል።

የከተማውን ሰላምና ጸጥታ ለማረጋገጥ በ7/24 የሥራ ባህል አጠቃላይ መዋቅሩን በማስተባበር የተመዘገበውን ተጨባጭ ለውጥ በማስቀጠል ለ2019 በጀት ዓመት የተቀመጡ ግቦችን በላቀ መንገድ በመፈጸም ብሎም በቀጣዮቹ 90 ቀናት የተለየ ትኩረት የሚሹ ተግባራትን በመለየት በተቀናጀ የፀጥታ ስምሪት በመስጠትና የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ማስቀጠል እንደሚገባ በዕቅድ ውይይቱ ተገልጿል ።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ባለፉት ጊዚያት የተከናወኑ ተግባራትን በቀጣይ ዘጠና ቀናት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

በዕቅድ የተያዙ ስራዎችን ለማሳካትና ለማስቀጠል የተጓደለውን በማረምና አመርቂ ውጤት ለማምጣት በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚገባም ገልፀዋል።

የፀጥታ መዋቅሩ ሰላምን እንደ የጋራ ኃላፊነት በመውሰድ በቅንጅት በታማኝነት፣ በተጠያቂነትና በሕዝብ አገልጋይነት መንፈስ በጋራ መስራትና ፣ ለከተማችን ዘላቂ ሰላምና ደኅንነት የተረጋገጠባት ከተማነቷን በማስቀጠል በትጋትና በቁርጠኝነት የዕቅዱን ተፈፃማነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ቢሮ ኃላፊዋ አሳስበዋል።

የዕቅዱ መነሻ ዋና ተግባራት በተመለከተ አቶ ማስረሻ ሀብቴ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የዕቅድና በጀት ዝግጅትና አፈጻጸም ዳይሬክትሬት ዳይሬክተር ሲያብራሩ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች የአፍሪካ ቀንድ የጸጥታ ሁኔታ፣የሀገራችን ወቅታዊ የጸጥታ፣የከተማ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ የውስጥና የውጪ የጠላት ሀይሎች ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ በተመለከተ ሲሆን ዳይሬክተሩ በግብ ሲያስቀምጡ እንዳሉት የሰላም ግንባታ ስራዎችን በተቀናጀ እና በላቀ የህብረተሰብ ተሳትፎ በመምራት ሰላምን ማስቀጠል፣የተቋም አቅም ግንባታ ስራዎች ተግባራዊ ማድረግ፣የሰላም እሴት ስራዎች ተሳትፎን ማላቅ፣የሰላም ሰራዊት ምልመላ ግንባታና ስምሪት ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል፣ወንጀልና ተያያዥ ሕገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈጸሙ የቅድመ ወንጀል የመከላከያና የጸጥታ ሀይሎችን አቅም ማሳደግ፣የወንጀል መከላከል ስራን በማሳካት የወንጀል ምጣኔን መቀነስ በወንጀለኞች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ እንደሆነ ተብራርቷል።

በመጨረሻም በዕቅዱ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሄዶ የአፈፃፀም አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79