የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀሙን ገምግሞ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀሙን ገምግሞ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የሩብ አመቱን አፈፃፀም ከአጠቃላይ የቢሮው መዋቅር ገምግመው የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ቢሮው በቀጣይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራቸውን ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችም ቢሮ ኃላፊዋ ሲሰጡ :-
* የተቋም ግንባታን ለማጠናከር አጠቃላይ የሰው ኃይልና ግብዓት በማሟላት ምቹ የሥራ ሁኔታ መፍጠር
*የአገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ማድረግና ስማርት ኦፊስን ተግባራዊ ማድረግ ፣ የዜጎችን እርካታ ማሳደግ
* የተጠያቂነት ሥርዓትን በመዘርጋት ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን መታገል
* ሕዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የሰላም ሰራዊትና የግል ጥበቃ ኃይል ምልመላን ማጠናከር፣ መረጃን በዳታቤዝ መሰነድና ለተልዕኮ ዝግጁ ማድረግ
*የማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶች የሰላም ዕሴት ግንባታ አቅም እንዲሆኑ ማድረግ
*የሰላም ዕሴት ግንባታ ስራዎችን ማጠናከር ፤የሀይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራትና በወል ትርክቶች የሚያምን ማህበረሰብ መፍጠር
*የቅድመ ወንጀል መከላከልና የስጋት ልየታ ሥራዎችን ማጠናከር
* የፀረ ሰላምና የፀጉረ ለውጥ ኃይሎችን እንቅስቃሴና አዝማሚያ በየጊዜው መከታተልና በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ቅብብሎሽ በማድረግ የቅድመ መከላከል ስራዎችን መስራት
* የኢኮኖሚ አሻጥርን መከላከልና ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነትን መከላከል
*የህገወጥ የንግድ ስርአትን በመቆጣጠር በተለይም የድጎማ ምርቶች ከደላላ ነፃ በሆነ መልኩ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ
*ለከተማዋ ሰላም፣ ደህንነትና የሕዝብ እርካታ ማረጋገጥ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።
በቀጣይም ከፀጥታ ተቋማት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር፣ ማህበረሰብ ተኮር ውይይቶችን ማስፋፋትና የሕዝብን በፀጥታ ስራዎች ተሳትፎ ማሳደግ እና የተቋማዊ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምን በማጎልበት፣ የተቋም ሪፎርምና የክፍተት ዳሰሳ ስራዎችን በማከናወን፣ የሽግግር ፍትህና የምክክር ኮሚሽን አጀንዳዎችን ወደ ተግባር በመቀየር የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ እንደሚሰራም ተጠቁሟል።