የፀጥታና የደህንነት ስራዎች በትኩረት በመሰራታቸው የአደባባይ ኩነቶች ሰላማዊ ሁነው እንዲያልፉ በማድረግ ከተማችን አዲስ አበባ የብሔር ብሔረሰቦች መገለጫ ከተማነቷን ማረጋገጥ ተችሏል።
የፀጥታና የደህንነት ስራዎች በትኩረት በመሰራታቸው የአደባባይ ኩነቶች ሰላማዊ ሁነው እንዲያልፉ በማድረግ ከተማችን አዲስ አበባ የብሔር ብሔረሰቦች መገለጫ ከተማነቷን ማረጋገጥ ተችሏል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የተጠሪ ተቋሙ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርት ከማዕከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ አመራሮች ጋር ግምገማዊ መድረክ አካሂዷል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት በተያዘው በጀት ዓመት በአንደኛ ሩብ አመት የቅድመ ወንጀል መከላከል ፣ የህግ ማስከበርና ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር የወንጀል ምጣኔን በእጅጉ መቀነስና የነዋሪውን በሰላም ወጥቶ መግባት ማረጋገጥ መቻሉን ገልፀዋል።
ኃላፊዋ አክለውም በመስከረም ወር የተከበሩ የአደባባይ በዓላትና ሁነቶች ፍጹም ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ የተደረገበት ፣ አዲስ አበባ የቱሪስት መዳረሻነቷ የተረጋገጠበት፣ ህብረ ብሔራዊነትና አንድነት ጎልቶ ለአለም ህዝብ የታየበት ፣ የከተማውን ነዋሪ የሰላም ባለቤት ማድረግ የተቻለበት መሆኑን አንሰተው የሽብር ሀይሎችን ሴራ በማክሸፍ ከከተማውና ከአጎራባች ከተሞች የፀጥታ አካላት ጋር ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
ነዋሪው በወንጀል መከላከልና በህግ ማስከበር ዙሪያ የግንዛቤ ማስረጽ ስራዎች መሰራታቸውን ያነሱት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ የወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ስራዎች የደንብ ጥሰትና ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግና የኢኮኖሚ አሻጥርንና ሰው ሰራሽ የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር የወንጀል ምጣኔን መቀነስ መቻሉን አብራርተው በቀጣይ ተቋም ግንባታን ማጠናከርና በከተማችን እየተመዘገበ ያለውን የሰላም የፀጥታና የደህንነት ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ መስራትና ማስቀጠል አንደሚገባ አሳስበው የኢትዮጲያን ስልጣኔ ለመገንባት ዝግጁነትን ወስዶ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ እንዳሉት በሩብ አመቱ በሁለቱም ተቋማት የተሰሪ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ጠቁመው በተለይም ህዝብን የሰላም ባለቤት በማድረግ ፣ የደንብ ጥሰቶችን በመከላከልና በማስከበር ፣ የተቋም ግንባታ ስራ ፣ የሰላም እሴት ግንባታ አንፃር ውጤታማ ሰራ መሰራቱን አንስተው የነበሩ ጥንካሬዎችን አልቆ ለመፈፀም በጊዜ የለኝም መንፈስ በንቃትና በቅንጅት በመስራት የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎችም የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራን ለማጠናከር የመረጃ ምንጮችን መጠቀምና የመረጃ ቅብብሎሽን ማዘመን ፣ ህገወጥ ድርጊቶችን ከመከላከል ፣ የኢኮኖሚ አሻጥርን ከመቆጣጠርና እርምጃ ከመውሰድ አንፃርና መሰል የፀጥታና የደህንነት ስራዎችን የመጡ ውጤቶችን በማስቀጠል አልቆ መፈፀም ላይ በትኩረት እንደሚሰሩና አልፎ አልፎ የሚታዩ ውስንነቶችና ጉድለቶችን አንስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79