የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክር ቤት ፀድ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክር ቤት ፀድቆ አዲስ ባቋቋመው የተቋማት አደረጃጀትና አሰራር መሰረት አገልግሎት አሰጣጥን ለተገልጋይ ምቹ ለማድረግ ተቋማትን መልሶ አደራጅቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክር ቤት ፀድቆ አዲስ ባቋቋመው የተቋማት አደረጃጀትና አሰራር መሰረት አገልግሎት አሰጣጥን ለተገልጋይ ምቹ ለማድረግ ተቋማትን መልሶ አደራጅቷል።

በተለያዩ ተቋማት ተበታትነው የነበሩትን ወደ አንድ ተቋም እንዲሰበሰቡ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በጎ ፈቃድና ህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ይሰጥ የነበሩና በተመሳሳይም በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ተግባራዊ የሚደረጉ አገልግሎቶችን የማዋሀድ ስራ ተሰርቷል።

በዚህም መሰረት በህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ሲሰጣቸው የነበሩ የተወሰኑ አገልግሎቶች ማለትም የህብረተሰብ ተሳትፎና የሰላም እሴት ግንባታ ፣ የህዝብ የቅጥር ጥበቃ ፣ የፀጥታ ስጋት ልየታና የሰላምና ፀጥታ የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት በከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አገልግሎት እንዲሰጥ በተወሰነው መሰረት የተቋማቱ ማኔጅሜንት አባላት ተወያይተዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በከተማ አስተዳደሩ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት አገልግሎቶችን ወደ አንድ ማዕከል በማምጣት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ለመጀመር የጋራ አድርጎ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀው የሚያስፈልጉ የሰው ሀይልና መሰል ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

በቀጣይ ጥቂት ቀናት ሙሉ በሙሉ የርክክብ ስራዎች ተጠናቀው አገልግሎቶቹ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ መሰጠት እንደሚጀመሩ ተመላክቷል።

መስከረም 29/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79