የፀጥታና የደህንነት ስራ በትኩረትና በቅንጅት መሰራት በመቻሉ በከተማችን የወንጀል ምጣኔን በመቀነስ በርካታ ኩነቶች በውጤታማነት ማከናወን ተችሏል።
የፀጥታና የደህንነት ስራ በትኩረትና በቅንጅት መሰራት በመቻሉ በከተማችን የወንጀል ምጣኔን በመቀነስ በርካታ ኩነቶች በውጤታማነት ማከናወን ተችሏል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ :- የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት በአንደኛ ሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎችን የቢሮው ማኔጅመንት ከአጠቃላይ ዳይሬክቶሬቶች ጋር ውይይት አድርጓል። በዚህ ወቅት በበጀት ዓመቱ አንደኛ ሩብ ዓመት በቅድመ ወንጀል መከላከል ፣ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ሂደትና የፀጥታ መረጃ ልውውጥን በማዘመን ረገድ ፣ የኦፕሬሽን ስራዎችና የመረጃ ተደራሽነትን ከማስፋትና ሌሎች የተቋሙ ተልዕኮዎች አንፃር ውጤታማ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ለዚህም የቅንጅት ስራዎች መኖር ፣ የአመራር ቁርጠኝነትና የሰራተኛው የላቀ አፈፃፀም መሆኑን ገምግሟል ።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት በቢሮው በበጀት ዓመቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ከመፈፀም ባሻገር በወቅታዊ ጉዳዮችን ላይ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።
ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም የታዩ ጥንካሬዎችን በማጠናከር አልቆ ለመፈፀም ራስን ዝግጁ ማድረግ ፣ ህብረተሰብን ማዕከል ያደረገ የፀጥታና የደህንነት ስራዎችን ማጠናከር ፣ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራን ማላቅ ፣ የመረጃ ልውውጥ ስርአትን ማዘመንና ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የከተማውን ሰላምና ደህንነት የማረጋገጥ፣ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በእሴት ግንባታ ዙሪያ ትኩረት መስጠትና ቅንጅታዊ ስራን ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበው በቀጣይም የተቋም ግንባታ ስራዎችን ፣ የሰላም እሴት ግንባታን ማጠናከር ፣ የፀጥታ መረጃ በማዘመንና በማላቅ ለኦፕሬሽን ዝግጁ ማድረግ ፣ የአደረጃጀት ስራዎችን ማጠናከርና የማህበረሰብ አቀፍ ውይይቶችን መደገፍ የሰላም ሰራዊቱን ማብቃትና የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
በግምገማው ወቅት ተቋሙ በዕቅድ የያዛቸውን አልቆ ከመፈፀም ባለፈ ህብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ የፀጥታ ፣ የቅድመ ወንጀል መከላከልና የኦፕሬሽን ስራዎች እንዲሁም የከተማውን ሰላምና ደህንነት በማረጋገጥ ሂደት ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸው የተመላከተ ሲሆን በተለይም በሩብ ዓመቱ መጨረሻ በከተማው የተከናወኑ የአደባባይ ሀይማኖታዊና ህዝባዊ በአላት ያለፀጥታ ስጋት ማለፍ መቻሉ ማሳያ መሆኑ ተገልጿል።
የቢሮው የበጀት ዓመቱ የአንደኛ ሩብ አመት የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተሰጥቷል።
መስከረም 29/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79