ለሀገር ግንባታና ለብሔራዊ መግባባት ሴቶች ሀላፊነትን መውሰድ እንደሚገባቸው ተገለፀ።
ለሀገር ግንባታና ለብሔራዊ መግባባት ሴቶች ሀላፊነትን መውሰድ እንደሚገባቸው ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የከተማውን ሰላም በማስከበር ሂደት ውስጥ ሴቶች አጋዥ የፀጥታ ኃይል በመሆን ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ሴቶች ለሀገር ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ያላቸው ሚና በሚል ርዕሰ "የሰላም ባለቤትነት ለሴቶች ለሰዊና ጤናማ ማህበረሰብ ግንባታ" ላይ ውይይት ተካኒዷል።
አቶ አዲስ ዘውዴ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ በውይይቱ ላይ እንዳሉት በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠርና ሰላም ወሳኝ መሆኑን አንስተው በዚህ ሂደት ውስጥ ሴቶች አይተኬ ሚና አላቸው ብለዋል። ኃላፊው አክለውም የሰላም ግንባታን በማጠናከር ፣ አካባቢን በመጠበቅ እርስ በርስ በመግባባትና አብሮ በመኖር ደረጃ ከሌላው በበለጠ ሴቶች ሀላፊነትን ወስደው እየሰሩ ስለሆነ እሱን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባልም ሲሉ ተደምጠዋል።
ሀላፊው አያይዘውም ሴቶች በሀገር ግንባታና ላይ በመሳተፍ ሀገራችን ያለችበትን የብልጽግና ጉዞ ወደ ፊት በማራመድ የቤት የጎረቤት የአካባቢ ብሎም የሀገር ሰላም እንዳይደፈርስ በማድረግ ስለ ሰላም በመወያየት በሀገር ጉዳይ ላይ በኔነት ስሜት ነገሮችን ማስተዋል እንደሚገባና ለሀገር ሰላም መጽናት በይበልጥ ሴቶች ሀላፊነትን መውሰድ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
አቶ ሙሉቀን እንየው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሰላም እሴት ግንባታ ብዝሀነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለሀገር ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ያላቸው ሚና በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ "የሰላም ባለቤትነት ለሴቶች ለሰላማዊና ጤናማ ማህበረሰብ ግንባታ" ላይ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ሰላም የማኅበረሰብ ልማት፣ የሀገር ግንባታ፣ የዲሞክራሲ ሥርዓትን ማጠናከርና ዘላቂ የልማት ውጤት ለማረጋገጥ መሠረት በመሆኑ ሰላም የግጭትና የጦርነት አለመኖር ብቻ ሳይሆን የሰዎች መብት የሚከበርበት የተለያዩ ማኅበረሰቦች በመከባበር የሚኖሩበት ልዩነቶች በውይይት የሚፈቱበትና ሁሉም ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉበት መሆኑን ገልፀው
በዚህ ረገድ ሴቶች ሰላምን በመጠበቅ ግጭትን በመከላከል በቤተሰብና በማኅበረሰብ ውስጥ መተሳሰብን በማጠናከር በብሔራዊ መግባባት ሂደቶች በመሳተፍና የሀገር ግንባታ በማበርከት ወሳኝ ሚና አላቸው ብለዋል።
አቶ ሙሉቀን አያይዘውም ሴቶች የሰላም ተጠቃሚዎች ብቻ ሳይሆን የሰላም ባለቤቶች አስተዋፅዖ አድራጊዎችና ውሳኔ ሰጪዎች አድርጎ ማብቃት ያስፈልጋል በማለት አብራርተዋል።
ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው የሰላም ጉዳይ በይበልጥ ደግሞ የሰላም እጦት ሲኖር ቅድሚያ ተጎጂ ሴቶች ስለሆኑ ለራስ ብሎም ለሀገር ሰላም መገንባት በጋራ እንደሚሰሩ ሀሳባቸውን ገልጸዋል ።
ውይይቱ በቀጣይ ሳምንትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል ።
መስከረም 29/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79