"በከተማችን አዲስ አበባ የቅድመ ወንጀል መከላከ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

"በከተማችን አዲስ አበባ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎች በትኩረት በመሰራቱ የወንጀል ምጣኔ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ መቀነስ ተችሏል"።

"በከተማችን አዲስ አበባ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎች በትኩረት በመሰራቱ የወንጀል ምጣኔ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ መቀነስ ተችሏል"።

አቶ ተስፋዬ ደንድር :- የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማውን ሰላም በማረጋገጥ ፣ የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ ፣ የነዋሪዎችን በሰላም ወጥቶ መግባትና ለማረጋገጥና የተጀመሩ የልማት ስራዎች ለታለመላቸው ግቦች እንዲውሉ የተቀናጀ ስራ እየሰራ ይገኛል። በዚህም የቢሮው የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅንጅት እንዲሁም ከህብረተሰቡ ጋር በትብብር በበጀት ዓመቱ የአንደኛ ሩብ አመት ውጤታማ ስራዎችን መስራት መቻሉን አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት ገልጿል።

አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት የዛሬ ሰላም መሆን ለነገ ሰላም ዋስትና የሌለው በመሆኑ የፀጥታና የደህንነት ብሎም የወንጀል መከላከል ስራዎች ላይ ዝግጁ በመሆን በየዕለቱ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለውም የታዩ ውጤቶች አልቆ ለመፈፀም በትጋትና በንቃት መስራት ይጠበቃል ብለው ከአጎራባች ከተሞችና ከፀጥታ አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ፣ የቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ፣ የፀጥታ ስጋቶችን መለየት ፣ የመንገድ ላይ የካሜራ ገጠማ ስራዎች ማስፋትና የውስጥ ለውስጥ የመንገድ መብራቶችን እንዲኖርና ጨለማ ቦታዎች በብርሀን እንዲሞሉ ማድረግ ላይ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው አሳስበዋል።

የፀጥታና ኦፕሬሽን እንዲሁም የቅድመ ወንጀል መከላከል ዙሪያ በበጀት ዓመቱ በአንደኛ ሩብ አመት የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት ያቀረበው የዘርፉ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳምጠው አያሌው የወንጀል ምጣኔን ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀር መሻሻል መታየቱን አብራርተው በመደበኛ የፀጥታ ስራ አካባቢዎችን ከጨለማ ነፃ በማድረግ ወንጀልንና ወንጀለኞችን ከመከላከል አንፃር እንዲሁም በተለይም በከተማው የተከበሩ የአደባባይ ሀይማኖታዊና ህዝባዊ በአላትና የተከናወኑ ኩነቶች ያለፀጥታ ስጋት መከናወን እንዲችል ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በከተማው የተጀመሩ የልማት ስራዎች በውጤታማነት መጠናቀቅ መቻሉ ፣ የተከናወኑ የአደባባይ በአላትና የመንግስት ምስረታ ያለፅጥታ ስጋት መከናወኑ የፀጥታ መዋቅሩ በቅንጅት መስራት በመቻሉና ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ የተሰራበት አግባብ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም ይህን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተው የነበሩ ክፍተቶችና መስተካከል ያለባቸውን አንስተው አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድርን ጨምሮ ከመአከል እሰከ ወረዳ የዘርፉ ዳይሬክቶሬቶች ፣ አስተባባሪዎች ፣ ቡ/መሪዎች ፣ባለሙያዎችና የኤጀንሲ ባለቤቶች ተሳትፈዋል።

መስከረም 29/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።