"በከተማችን አዲስ አበባ የንግድ ስርአቱን በመቆጣጠር ፣ ጥራት ያለው የፍጆታ ምርት አቅርቦትን በማሳደግና ህገ-ወጥነትንና የኑሮ ውድነትን የመከላከል ስራ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል"።
"በከተማችን አዲስ አበባ የንግድ ስርአቱን በመቆጣጠር ፣ ጥራት ያለው የፍጆታ ምርት አቅርቦትን በማሳደግና ህገ-ወጥነትንና የኑሮ ውድነትን የመከላከል ስራ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል"።
ክቡር አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ:- የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ
የአዲስ አበባ ከተማ የገበያ ማረጋጋትና የህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ኃይል ገበያውን ከማረጋጋትና ህገወጥ ንግድን ከመቆጣጠር አንፃር ባለፉት ሦስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
ግብረሀይሉ በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ሶስት ወራት የተሰሩ ስራዎችን ሲገመግም እንዳለው በከተማው ውስጥ ህገወጥ የንግድ ስርአትን በመቆጣጠርና ያለደረሰኝ ግብይት የሚያካሂዱ አካላትን ወደ ህጋዊ ስርአት በማስገባትና አሰራርን በማስጠበቅ ህብረተሰቡን ከኑሮ ውድነት ለማላቀቅ ውጤታማ ሰራ መሰራቱን በአጭር ሪፖርት ያሳየ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎችም በተከናወኑ ስራዎች የተመዘገበ ውጤት በቅንጅት መሰራት በመቻሉ መሆኑን አንስተው በአሰራር ሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ክቡር አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ በከተማው የንግድ ስርአትን መቆጣጠርና የገበያ ሁኔታን በማረጋጋት የህብረተሰብን የኑሮ ጫናን ማቅለል የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን አንስተው በዚህም ባለፉት ወራት ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
አቶ ሳሙኤል አክለውም የገበያን ሁኔታ በዘላቂነት ለማረጋጋትና አምራቹንና ሸማቹን በማቀራረብ የህብረተሰቡን ፍላጎት መሰረት በማድረግ የግብረሀይሉ አባላት በጥብቅ ዲሲፕሊን በቅንጅት 24/7 በትኩረት መስራት እንሚገባ አፅንኦት ሰጥተው በቀጣይ ያለንግድ ፈቃድ የሚሰሩ አካላት ፣ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈፅሙና ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የንግድ ስርአቱን ለማዘመን መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት በግብረ ሀይሉ የንግድ ስርአት ቁጥጥርና የገበያ ማረጋጋት ላይ የተሰሩ ስራዎች ለውጥ የታየባቸው መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። ኃላፊዋ አያይዘውም የንግድ ስርአቱን በመቆጣጠር ሂደት ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈፅሙ አካላትን አስተማሪና አሰራርን የጠበቀ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ገልፀው ይህም የኑሮ ውድነት ለማቃለልና ሰው ሰራሽ የዋጋ ግሽፈትን ለመከላከል ወሳኝ መሆኑን አንስተው ግብረ ሀይሉ በትኩረት የሚሰራበት መሆኑን አብራርተዋል።
ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ባለፉት ሶስት ወራት ከአጎራባች ከተሞች ጋር በቅንጅት በመሠራቱ በተለይም ከበአላት ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የዋጋ ግሽፈቶችን ማስቀረት መቻሉን አንስተው በቀጣይም የፍጆታ ምርቶችን አቅርቦት በማሳደግና ህገወጦችን በመቆጣጠር እንዲሁም የደላላ ጣልቃ ገብነት በማስቀረት የኑሮ ውድነትን የማረጋጋት ስራ ከነበረው በላቀ ውጤታማነት ለመስራት ዝግጁነት መውሰድና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመድረኩ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ የሚገኙ የገበያ ማረጋጋት፣ ህገ-ወጥ የንግድ ቁጥጥር ግብረ-ኃይል አባላት ተሳትፈዋል።
መስከረም 28/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79