"የመረጃ ልውውጥን በማዘመንና በማጠናከር በከተማዋ የሚስተዋሉ የወንጀል አዝማሚያዎችን መቀነስ ተችሏል"።
"የመረጃ ልውውጥን በማዘመንና በማጠናከር በከተማዋ የሚስተዋሉ የወንጀል አዝማሚያዎችን መቀነስ ተችሏል"።
ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ :- የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ
በተያዘው በጀት ዓመት ህብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ የፀጥታና የደህንነት ስራ መስራት በመቻሉ የፀጥታ ስጋቶችን በመቀነስ የከተማን ደህንነት በማረጋገጥ የህብረተሰቡን በሰላም ወጥቶ መግባት ማረጋገጥ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ መረጃ ዘርፍ የበጀት ዓመቱን የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት አስታውቋል።
ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትልና የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ በ1ኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ የፀጥታ መረጃ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ከፀጥታ አካላትና ከአዲስ አበባ ከአጎራባች ከተሞች ጋር የተጀመሩ የቅንጅት አሰራሮች መሻሻሎችን እያስመዘገቡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይም ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት የሰላምና ፀጥታ ስራዎች መስራት ፣ የስጋት ቦታዎችን በወቅቱ መለየት፣ ሰላማዊ እንቅስቃሴዎች ጤናማና ሰላማዊ መሆናቸውን በመከታተል ተገቢ ትንተና ማካሄድ፣ እንዲሁም የሚገኙ መረጃዎችን በጥራትና በወቅቱ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ዋና ሥራዎች መካከል መሆናቸው ሀላፊው አክለው ገልጸዋል።
የግምገማው ዋና ዓላማ የፀጥታ መረጃ አሰራሩን በማጠናከርና በማዘመን የሚሰበሰቡ መረጃዎችን በወቅቱ መቀበል፣ ማጣራት፣ መተንተንና ለሚመለከተው አካል በጥራት ማቅረብ እንዲቻል የአሰራር ሂደቱን ማሻሻል ነው ሲሉ ወ/ሪት ዳግማዊት ቸርነት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ መረጃ ዘርፍ፣የፀጥታ መረጃ አስተዳደር የክትትል ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሪፖርቱ ገልጸዋል።
በግምገማው የታዩ ጥንካሬዎችና ክፍተቶች በዝርዝር የተነሱ ሲሆን፣ የመረጃ ቅብብል በወጥነት አለመከናወን፣ ወቅታዊ መረጃዎችን በጊዜና በጥራት አለመላክ እንደ ዋና ክፍተቶች ሲቀርቡ፣ተልዕኮና ኃላፊነቶችን በግልጽ በመረዳት በተገቢው ሁኔታ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ መፈጸም እንደሚገባ ዳይሬክተሯ አብራርተዋል።
በመድረኩም በአፈፃፀም ሪፖርቱ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል።
መስከረም 28/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79