የአገልግሎት አሰጣጥን በቴክኞሎጂ በማዘመን ለህብ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአገልግሎት አሰጣጥን በቴክኞሎጂ በማዘመን ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ተገቢ እንደሆነ ተገለፀ።

የአገልግሎት አሰጣጥን በቴክኞሎጂ በማዘመን ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ተገቢ እንደሆነ ተገለፀ።

አለም የደረሰችበትን ቴክኖሎጂዎች ወደ ሀገርና ከተማ በማምጣትና ዘመኑን ያዋጀ ግብአቶችን በመጠቀምና ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎትን መስጠት እንዲገባ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከቢሮው ባለድርሻ አካላት ከሲቪል ማህበራት ጋር ውይይት ባካሄደበት ወቅት ገልጿል።

አቶ ጌታሁን አበራ አዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ እንዳሉት ቢሮው የሚሰጣቸውን አገልግሎትች ከቅሬታ ነፃ በሆነ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ስልቶች ቀይሶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት አገልግሎቶችን የማዘመንና በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተው ለሀገር ግንባታና ለከተማ ደህንነት መረጋገጥ ህብረተሰብን ማዕከል ያደረገ የሰላምና የደህንነት ስራዎች በቴክኖሎጂ የተደገፉ በማድረግ እንዲሁም ነዋሪዎች ባሉበት ቦታ ሁነው በፀጥታ ዙሪያ ቅሬታ የሚያቀርቡበት የቅሬታ አፈታት መንገድ በመዘርጋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

አማካሪው አያይዘውም ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ በጋራ በመስራት ሞያተኛው በየደረጃው የተሟላ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ችግሮችን በማዳመጥና ምላሽ መስጠት ሲቻል የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲፍጠኑ ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የፈጠነ ምላሽ መስጠትን ተገቢ መሆኑንም ጠቁመው ፍትሀዊነት እንዲረጋገጥ ሚዛናዊ ቀልጣፋ አገልግሎት መሰጠት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

ወ/ሮ አለም ጸሀይ ማሞ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሪፎርም እና አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ዳይሬክተር ለውይይት የሚሆነውን ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት ምላሽና ማብራሪያም ተሰቶበታል።

መስከረም 28/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።