በሰላም እሴት ግንባታ እና በሰው ተኮር ስራዎች ዙሪያ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት ውጤታማ ስራዎች መስራት መቻሉ ተገለፀ።
በሰላም እሴት ግንባታ እና በሰው ተኮር ስራዎች ዙሪያ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት ውጤታማ ስራዎች መስራት መቻሉ ተገለፀ።
በከተማው ውስጥ ሀይማኖታዊና ህዝባዊ የአደባባይ በአላት ባህላዊ ትውፊታቸውንና ሀይማኖታዊ ስርአቱን ጠብቆ ማለፍ እንዲችሉ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በሰላም እሴት ግንባታና መሰል ተግባራት ላይ በቅንጅት በመስራቱ ውጤታማ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት ገለጿል።
አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የሀይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከሀይማኖት ተቋማት ጋር የቅንጅት ስራዎች ፣ በብሔራዊ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ፣ የሰው ተኮር ስራዎች እንዲሁም የሰላም እሴት ግንባታዎች ላይ ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት መሰራቱንና በዚህም ተጨባጭ ውጤት የተያበት አግባብ መኖሩን ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም በዲጂታል ሚዲያ የጋራ እሴቶችን የሚሸረሽሩ መረጃዎችን ለመግታትና የጋራ እሴቶችን ለማጎልበት የሚያስችል የዲጂታል እሴት ግንባታ ስራ በተለይም ከወጣቶች ጋር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አንስተው በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥልና በትኩረት እንዲሰራ አፅንኦት ሰጥተዋል።
በሀይማኖትና በሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ በበጀት ዓመቱ በ1ኛ ሩብ አመት የተከናወነ የተግባር አፈፃፀም ሪፖርቱን ያቀረበው የዘርፉ ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ህብረተሰብን ማዕከል ያደረገ የሰላም እሴት ግንባታ ላይ በርካታ ስራዎች መስራት መቻሉን ገልፀው በተለይም ከወጣቶች ጋር የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች በመሰራቱ የጋራ እሴቶችን በማጠናከር የእርሰ በርስ ግንኙነትን ማላቅ መቻሉን አብራርተዋል ።
አያይዘውም ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በቅርበት የተሰራበት አግባብ መኖሩን አንስተው በዚህም በከተማችን የተከበሩ የአደባባይ በአላት ሀይማኖታዊ እሴቱንና ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ እንዲያልፍ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ የዘርፉ ከመአከል እስከ ወረዳ ያሉ ሰራተኞች በሩብ አመቱ በቅንጅትና የሚሰጡ አቅጣጫዎች መሰረት በማድረግ ውጤታማ መሆናቸውን አንስተው በቀጣይ ቢስተካከሉ ያሏቸውን ሀሳቦች አንስተው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በመጨረሻም የተቋም ግንባታ ስራ ፣ ህብረተሰብን ማዕከል ያደረገ የሰላም እሴት ግንባታ ፣ የዲጂታል ሚዲያ የእሴት ግንባታ ላይ ፣ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር የቃልኪዳን ቤተሰብ ትስስር ፣ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በቅርበት መስራትና የሀይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታን ማጠናከር የሚያስችሉ የትኩረት አቅጣጫዎችኝ አቶ ብርሀኑ ረታ የቢሮው ምክትልና የዘርፉ ሀላፊ ሰጥተዋል።
መስከረም 27/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79