ተቋማዊ አቅምን በማጎልበት ፤ የስራ ቅልጥፍናን ለማዘመንና የዜጎችን እርካታ ለማሳደግ አገልግሎቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።
ተቋማዊ አቅምን በማጎልበት ፤ የስራ ቅልጥፍናን ለማዘመንና የዜጎችን እርካታ ለማሳደግ አገልግሎቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እየሰጠ ሲሆን ይህን አልቆ ለመፈፀም የስማርት ኦፊስና የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብን ከወረቀት ነፃ በሆነ በቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለመአከል ሰራተኞች ሰጥቷል።
በግንዛቤ ማስጨበጫው ወቅት የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት፣ የስማርት ኦፊስና የቅሬታ አቀባበልና አፈታት ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የታለመው ከወረቀት አሰራር በመላቀቅ ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው የአሰራር ሂደትን ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።
ሀላፊው አክለውም የዲጂታል ቴክኖሎጂን በስራ ሂደቶች ውስጥ በስፋት በመጠቀም የወረቀት ስራን መቀነስ፣ የሰራተኞችን ጊዜና ጉልበት መቆጠብ፣የስራ ሂደትን ማቀላጠፍና የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል እንደሚቻልም ጠቁመው፣በተለይም ተገልጋዮች ለአገልግሎት በአካል በተደጋጋሚ ወደ ቢሮው መምጣት ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ፣ ጥያቄና ቅሬታቸውን በቀላሉ እንዲያቀርቡና ምላሽ እንዲያገኙ የሚያስችል የተሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት በመዘርጋት ቢሮው ወደ ስራ መግባቱን ጠቁመው ሰራተኛው ባገኘው ግንዛቤ በመጠቀም አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ መስጠት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የሰጡት ከጥበብ ዲዛይንና ቴክኖሎጂ ቡልዲንግ ካምፓኒ የአይቲ ሰፖርት ኦፊሰርና ቲም ሊደር አሰልጣኝ ወ/ት ፀደይ አሸናፊ ሲሆኑ፣ በስማርት ኦፊስና ቅሬታ አቀባበልና አፈታት ስራዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ በተቀላጠፈና በተደራጀ መልኩ ለመፈጸም የሚያግዝ ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በተለይም የወረቀት ስራን በመቀነስ ሂደቶች በአጭር ጊዜ እንዲፈጸም እና ወደ ዲጂታል አሰራር በማሸጋገር፣ የስራ ጊዜን መቆጠብ፣የስራ ጥራትን ማሻሻልና ተደራሽ የሆነ የቅሬታ አስተዳደር ስርዓት መፍጠር የስልጠናው ዋና ዓላማዎች መሆናቸው አሰልጣኟ ገልጸዋል።
በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች በተሰጠው ስልጠና ዙሪያ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በማቅረብ ያነሷቸውን ጉዳዮች በማስረዳትና በማብራራት በቂ ምላሽ ተሰጥቶ ስልጠናው ቀጣይነት እንዳለው ተጠቁሟል።
መስከረም 27/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79