በመርካቶና አካባቢው የደረሰኝ ቁጥጥርን በማጠናከ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በመርካቶና አካባቢው የደረሰኝ ቁጥጥርን በማጠናከር ህጋዊ የግብይት ስርዓት ለማስፈን በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ::

በመርካቶና አካባቢው የደረሰኝ ቁጥጥርን በማጠናከር ህጋዊ የግብይት ስርዓት ለማስፈን በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የህገወጥ ንግድ መከላከልና ደረሰኝ ቁጥጥር የጋራ ግብረሃይል ህጋዊ የግብይት ስርዓት ለማስፈን እየተሰራ ያለውን ስራ በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል::

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ እና የጋራ ግብረሃይሉ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በመርካቶና በአካባቢው ህጋዊ የንግድና የግብይት ስርዓት ለማስፈን የተጀመረው የተቀናጀ የቁጥጥርና ክትትል ስራ ተስፋ ሰጭ ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን ጠቅሰው ያለ ደረሰኝ ግብይትን በማስቀረት የኢ-መደበኛ የንግድ እንቅስቃሴን ለመቀነስ እየተሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጭ ውጤት እየተመዘገበበት ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል::

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በበኩላቸው የንግድና የግብይት እንቅስቃሴውን ስርዓት በማስያዝ የተረጋጋ ገበያ እንዲፈጠርና የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ የተጀመረውን ስራ የበለጠ ውጤታማ አድርጎ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል::

የጋራ ግብረሃይሉ አባላት በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ የደረሰኝ ቁጥጥርና ክትትል ስራውን በማጠናከር ህጋዊ ግብይት ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት አጠናክረን እናስቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል::

በውይይት መድረኩ ከላይ ከተጠቀሱ የስራ ሃላፊዎች በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እንዲሁም ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ስራው ያለበት ደረጃ ተገምግሞ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል::

መስከረም 26/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79