የ2019 ዓ.ም የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአል የህዝቦችን የእርስ በርስ ግንኙነት ባጠናከረና የሀገርን ከፍታ ባረጋገጠ መልኩ እንዲከበር
የ2019 ዓ.ም የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአል የህዝቦችን የእርስ በርስ ግንኙነት ባጠናከረና የሀገርን ከፍታ ባረጋገጠ መልኩ እንዲከበር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በሁሉም ክ/ከተሞች ለጥምር የፀጥታ ሀይሉ የምሽት የፀጥታ ስምሪት ተሰጥቷል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት ከተማችን አዲስ አበባ የለውጥ ጎዳና ላይ እንደመሆኗ የበርካታ ቱርስቶች መዳረሻ ሆናለች ብለው ይህን ውጤት ባላቀ መልኩ ውጤታማነቱን በማረጋገጥ የፀጥታ ስራን በቅንጅት በመስራት የምሰጋና ፣ የፍቅርና የአንድነት በአል የሆነውን ኢሬቻ በአልን ባህላዊ እሴትን በሚያጎላ መልኩ ተከብሮ እንዲያልፍ በርካታ የፀጥታና የደህንነት ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።
ኃላፊዋ አክለውም በአሉን ለማክበር ወደ ከተማችን የሚመጡ እንግዶችን በሰላም በአሉን አክብረው እንዲመለሱ በማድረግና በአሉ የህዝቦችን እርስ በርስ የመከባበርና አንድነትን ባጠናከረ መልኩ እንዲከበርና ሀገራዊ ፋይዳውን ባደመቀ መልኩ ተከብሮ እንዲያልፍ የፀጥታ መዋቅሩ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።
አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት በከተማችን የሚከበሩ የአደባባይ በአላቶች በሰላም ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱንና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ተከብረው እንዲያልፉ ውጤታማ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ ቀናት የሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአል ያለምንም የፀጥታ ስጋት በአሉን ለማክበር ወደ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶች በሰላምና በነፃነት እንዲያከብሩ ፣ በአሉ የህዝቦችን መከባበርና አንድነትን እንዲያጠናክር ማስቻልና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በንቃት መከታተልና በመጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የኢሬቻ በአል የምስጋና ፣ የፍቅር የመተሳሰብ በአል ነው ያሉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ ህዝቡ የሰላም ባለቤትና ሰላም ወዳድ እንደመሆኑ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅትና በንቃት በመስራት በአሉን ለማክበር ወደ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶችን በነፃነት እንዲያከብሩ የፀጥታ መዋቅሩ የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበው በአሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበር ህዝብን መአከል ያደረገ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
የፀጥታ ስምሪት የህዝብ እንቅስቃሴን በማስተባበር ፣ የትራፊክ ፍሰትን በማስተካከል፣ የወንጀልና የሌሎች ስጋቶችን በመከላከል በዓሉ ያለምንም ስጋት እንዲከበሩ ለማድረግ ዛሬ በሁሉም አቃቂ ቃልቲ ፣ በአዲስ ከተማና በልደታ ክ/ከተሞች የምሽት የፀጥታ ስምሪት ተሰጥቷል።
መስከረም 21/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79