"እሬቻ ለብሔራዊ መግባባት"
"እሬቻ ለብሔራዊ መግባባት"
የክረምቱ ወቅት አልፎ የፀሀይ መውጣትን ተከትሎ የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት ወጥቶ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርቡብት የገዳ ስርአት መገለጫ የሆነው የእሬቻ በዓል የህዝቦችን አንድነት ባጠናከረ ፣ የሀገርን ከፍታ በሚያሳይ ፣ ህብረብሔራዊ አንድነትን ባጎላ መልኩ እንዲከበርና በአሉን ለማክበር ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ እንግዶች በኢትዮጲያዊ ጨዋነት ተቀብሎ በማስተናገድ በአሉን በፍቅር ፣ በአንድነትና በወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸው ተገለፀ።
ይህን አስመልክቶ የአዲስ አበባና የሸገር ከተማ አስተዳደሮች የውይይት መድረክ አካሂደዋል።
ሌተናል ጀነራል አስራት ደኔሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና መምሪያ ዋና አዛዥ በውይይት መድረኩ ላይ እንዳሉት ኢትዮጲያ ካሏት ውብ የአደባባይ በአል አንዱ የእሬቻ በአል መሆኑን ገልፀው በአሉን ለማክበር ከተለያዩ አጎራባች ከተሞች ወደ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶችን በመቀበል ፣ በአሉ የፍቅር የአንድነትና የምስጋና የእርስ በርስ ግንኙነትን ባጠናከረ መልኩ እንዲሆን ነዋሪው ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል።
ጄነራሉ አያይዘውም ሰላምን በመጠበቅና የአደባባይ በአላት ያለፀጥታ ስጋት ተከብረው እንዲያልፉ ህዝቡ ሀላፊነቱን እየተወጣ በመምጣቱ ሰላማዊ ሀገርና ከተማ በመገንባት የህዝቦችን አንድነት ማጠናከር ተችሏል ብለው ይህን በማስቀጠል እጅ ለእጅ በመያያዝ የሰላምን ዋጋ በማጽናት የእሬቻ በዓል እንደሌሎቹ በዓላት ሁሉ በሰላም እንዲከበር በጋራ በመሆን ጸጉረ ለውጦችን በመቆጣጠርና ከተማውን ለማወክ የሚተጉ አካላትን ሀሳባቸው እንዳይሳካ ህዝቡ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመናበብና መረጃ በመስጠት ሁሌም አሸናፊ የሆነች ሀገርን ይበልጥ ነጻነቷን አረጋግጣ እንድትቀጥል የማድረግ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ እንዳሉት በአዲስ አበባ የሆራ ፊንፊኔ ብሎም በሆራ አርሰዲ ቢሾፋቱ ከተማ የሚከበረው የእሬቻ በአል ለሀገራችን ድምቀት እንዲሆንና እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ እንደመሆኑ በዓሉ የፍቅር የአንድነት የአብሮነትና የምስጋና መገለጫ በዓል የሚከበርበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዓሉ ሲከበር በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ የከተማው በመግባት በዓሉን የሚከበርበት ወቅት ስለሆነ እንግዶችን በሰላም ተቀብሎ በሰላም በመሸኝት የተሻለ አቀባበል በማድረግና ጸጥታውም አስተማማኝ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተናግዋል።
ኮምሽነር ተሻለ ኦብሴ የሸገር ከተማ የጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ በበኩላቸው ባለፍት በዓሎች በቅንጅት በመሰራቱ በርካታ የጸረ ሽብር የጠላት ሀይሎች ሴራን ማክሸፍ እንደተቻለ ሁሉ የበዓሉ አክባሪ በመምሰል አብሮ በመግባት የበዓሉን ድባብ ለማጥፋት የሚተጉ አካላትን ህብረተሰቡ በመገንዘብ አካባቢውን በመጠበቅ የተለየ ነገር ሲያይ አካባቢው ላይ ላለ የጸጥታ አካል ጥቆማ በመስጠት ለሰላም በመቆም በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ መግቢያና መውጫ በሮች አካባቢ በቂ ጥበቃ በማድረግ በኩል መንግስት ሰፊ ስራ እየሰራም እንደሚገኝ ገልጸው ህዝቡ አንድ በመሆን በዓሉን በሰላም ማክበር እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ አስተዳደርና የሸገር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ሀላፊዎች፣የሀይማኖት አባቶች፣ሀደ ሲንቂዎች ሚሊሻዎች ሌሎችም በርካታ አጋዥ የጸጥታ ሀይሎች ተገኝዋል።
የዘንድሮው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በደመቀ መልኩ እንዲከበር የፀጥታና የደህንነት ስራዎች ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።
መስከረም 21/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79