ወንጀልን በቅድመ መከላከል ላይ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለጸ።
ወንጀልን በቅድመ መከላከል ላይ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለጸ።
“የወጣቶች ኃይል ለሰላም፣ የወደፊት ዕጣ ፈንታችን በእጃችን” በሚል መሪ ሃሳብ ወንጀልን በተለይም የስርቆት ወንጀልን በበዓላት ወቅት ለመከላከል የህብረተሰቡ ተሳትፎና የህግ ማስከበር አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።
የኃይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ የሰላም ዕሴት ግንባታ የብዙኃን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙልቀን እንየው ለወጣቶች ግንዛቤውን ሲሰጡ እንዳሉት የወንጀል ሕግ ዋና ዓላማ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት እንዲሁም የንብረት ባለቤትነትን ማረጋገጥ ከመሆኑ ባሻገር ፣ ወንጀል ከተፈጸመ በኋላ ምርመራና የሕግ ሂደት ከማከናወን ይልቅ ወንጀል ከመፈጸሙ በፊት መንስኤዎቹን በመለየት በቅድመ መከላከል ላይ በመስራት ለሰላማዊ ኑሮ፣ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዲሞክራሲ ልማት ወሳኝ መሆኑ አመላክተዋል።
የህግ ማስከበር አካላትም በበዓላት ወቅት የሚከሰቱ የስርቆትና ሌሎች ወንጀሎችን ለመከላከል የጥበቃና የቁጥጥር ሥራዎችን በማጠናከር፣ ከህብረተሰቡ የሚመጡ የወንጀል ጥቆማ መረጃዎችን በመከታተልና ህግን በሚጥሱ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ በኢሬቻ በዓላት ወቅት ሰላማዊና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ከፊታችን የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ክንዲከበር ወጣቶች በጎ ፈቃደኝነትና በሰላም ሰራዊት ማገልገል፣ የበዓሉን ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴት መጠበቅ፣ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንዲሁም ከበዓሉ በኋላ አካባቢውን ማጽዳትና ማደራጀት እንዳለባቸው የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
መስከረም 20/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79