የኢሬቻ በዓል ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የሚ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የኢሬቻ በዓል ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የሚያስችለው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የፀጥታ ጥምር ግብረ-ኃይል አስታወቀ።

የኢሬቻ በዓል ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የሚያስችለው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የፀጥታ ጥምር ግብረ-ኃይል አስታወቀ።

​የክፍለ ከተማው የፀጥታ ጥምር ግብረ-ኃይል የ2019 የኢሬቻ በዓል በተረጋጋና ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ሙሉ ዝግጅት መደረጉን ገልጿል።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ በበኩላቸው፣ በዓሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በሁሉም አካባቢዎች የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪትን በማጠናከር የተጀመሩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።

​የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚና የሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አከበረኝ ወጋገን በሰጡት ማብራሪያ፣ የበዓሉን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በርካታ አደረጃጀቶችና ህብረተሰቡን ያሳተፉ ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ጠቁመው፣ በአሁኑ ወቅት በዓሉን በሰላም ለማክበር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በሙሉ በስኬት መጠናቀቃቸውን አብራርተዋል።