የፀጥታ መዋቅሩ የተቀናጀ የፀጥታ ስራ በመስራቱ የአደባባይ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲያልፉ ማድረግ ተችሏል።
የፀጥታ መዋቅሩ የተቀናጀ የፀጥታ ስራ በመስራቱ የአደባባይ በዓላት ሰላማዊ ሆነው እንዲያልፉ ማድረግ ተችሏል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው የሚከበሩ የአደባባይ ህዝባዊና ሀይማኖታዊ በአላት ያለፀጥታ ስጋት ሀይማኖታዊ ስርአቱን ፣ ባህላዊ እሴቱንና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ተከብረው እንዲያልፉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን በቀጣይም የኢሬቻ በአል ሀይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቆ እንዲያልፍ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥቷል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በመድረኩ ላይ እንዳሉት የፀጥታ መዋቅሩ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ ፣ በዓላት የሚከበሩባቸውን ቦታዎች ከስጋት ነፃ በማድረግና የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪት በመስጠት የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸው ገልፀው ፣ በተለይም የመስቀል ደመራ ቦታዎች ካለፈው ዓመት በተሻለ ሁኔታ ሰላማዊ እንዲሆኑ የተመዘገቡ ውጤቶች የህብረተሰቡና የፀጥታ አካላትን የጋራ ስራ ውጤታማ መሆኑን ገልፀዋል።
በበዓላት ወቅት የተገኙ ውጤቶችንም ለቀጣይ ስራ ግብዓት በማድረግ ፣ በተለይም በቅርቡ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ሰላማዊ ሆኖ እስኪጠናቀቅ ድረስ ስጋት የሚፈጥሩ አዝማሚያዎችን መለየትና ሌላ ተልዕኮ ይዘው ሊመጡ የሚችሉ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በመከታተል የቅድመ መከላከል ስራዎችን በትኩረት በመስራት ሁሉም የራሱን ተልዕኮ በተገቢው መወጣት እንደሚገባም ወ/ሮ ሊዲያ አክለው ገልጸዋል።
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ እንደገለጹት፣ ባለፉት የጳጉሜ፣ የአዲስ ዓመትና የመስቀል ደመራ በዓላት የተሰጡ ተልዕኮዎችን በተጨባጭ በመፈጸም የተገኘው ውጤት የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመው፣ ቀጣዩ የኢሬቻ በዓል ብዙ ተሳታፊዎችን የሚያሳትፍና ከከተማዋ ውጭ የሚመጡ እንግዶችም የሚበዙበት በመሆኑ የኦፕሬሽንና የመረጃ ስራዎችን በጥምረትና በቅንጅት በጥብቅ በመከታተል ለበዓሉ ሰላማዊ አከባበር የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በውይይቱም ወቅት የጳጉሜ ወር ጳጉሜ 3 የጽናት ቀን እና የመስቀል ደመራ አፈጻጸም ሪፖርት አቶ ተስፋዬ ደንድር ፣የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ ያቀረቡ ሲሆን ፣ በገለጻቸውም በአላቱ ሲከበሩ በሰላማዊና ፀጥታው በተጠበቀ መልኩ እንዲከናወን የተደረጉ የጋራ ሥራዎች ፣ የተመዘገቡ ውጤቶችና ያጋጠሙ ችግሮች አብራርተዋል።
በመጨረሻም የቀጣይ የእሬቻ በአል አከባበር የፀጥታና የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችና የደንብ ጥሰቶች እንዳይኖሩ የፀጥታ መዋቅሩ ከህዝቡ ጋር በቅንጅት መሰራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
መስከረም 19/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79