የ2019 የሆራ ፊንፊኔ እሬቻ በአል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ለአዲስ አበባና ለሸገር ከተማ ለጥምር የፀጥታ ሀይሉ የምሽት ስምሪት ተሰጠ።
የ2019 የሆራ ፊንፊኔ እሬቻ በአል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ለአዲስ አበባና ለሸገር ከተማ ለጥምር የፀጥታ ሀይሉ የምሽት ስምሪት ተሰጠ።
በአዲስ አበባ ከተማ በየአመቱ በመስከረም ወር መጨረሻ የሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ እሬቻ በአል በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚከበር ይታወቃል ። በአሉን ለማክበር ከተለያዩ አጎራባች ከተሞች ወደ ከተማዋ የሚገቡ በርካታ ህዞቦች ያሉ በመሆኑ እንግዶቹ ያለስጋት እርስ በርስ በመከባበርና አንድነት በሚያጠናክር መልኩ አክብረው እንዲያልፉ የፀጥታና የደህንነት ሁኔታን በመከታተል ጥብቅ ስምሪት የመስጠት ስራ እየተሰራ ይገኛል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ለአዲስ አበባና ለሸገር ከተማ ጥምር የፀጥታ ሀይል የሆራ ፊንፊኔ እሬቻ በአልን አስመልክቶ የምሽት የፀጥታ ስምሪት ተሰጥቷል።
አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት የመስቀል ደመራ በአል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ጥምር የፀጥታ ሀይሉ በቅንጅት በሰራው ስራና በፈጣሪ ዕርዳታ የሀገርን ገፅታ ከፍ ባደረገ መልኩ እንዲከበር ተችሏል ብለዋል። ከተማውን ለመረበሽ የሚጥሩ ሀይሎች በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ ሰላም ለማደፍረስ የሚሰሩ ግለሰቦችና ቡድኖችን ሴራ ቀድሞ በማክሸፍ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆኑን ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም ይህን የተቀናጀ የፀጥታ ስራ በማጠናከር ከፊታችን የሚከበረው በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በደመቀ መልኩ የሚከበረው የሆራ ፊንፊኔ እሬቻ በአል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር በቅንጅትና በመናበብ መሰራትና የሚመጡ እንግዶችን በሰላም በአሉን አክብረው እንዲመለሱ ማድረግ እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ እንዳሉት የአዲስ አበባና የሸገር ከተማ በጥምረት የሚሰሩት የፀጥታ ስራ የከተሞቹን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ መቻሉን አንስተው የፀጥታ ጥምር ሀይሉ የህዝብ ጋሻ የህብረተሰቡ አይንና ጆሮ በመሆን ለአካባቢያቸው ዘብ በመቆም የአንድነት ፣ የፍቅርና የምስጋና በአል የሆነውን የእሬቻ በአል ያለምንም የፀጥታ ስጋት እንዲከበር በንቃት መጠበቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
መስከረም 19/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79