"እሬቻ ለብሔራዊ መግባባት"
"እሬቻ ለብሔራዊ መግባባት"
ወጣቶች ኢሬቻን በሰላም ፣ በመከባበርና በኃላፊነት በማክበር የበዓሉን ባህላዊ እሴት ለትውልድ ከማስተላለፍ ባለፈ፣ ሰላምንና አንድነትን በማጠናከር ሚናቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የገዳ ስርአት መገለጫ የሆነው በዮንስኮ በማይዳሰስ ቅርስ የተመዘገበው የ2019 ዓ.ም የሆራ ፊንፊኔ እሬቻ በአል ፍፁም ሰላማዊ በሆነና ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ አንድነትን ባጠናከረና የሀገርን ገፅታ በሚገነባ መልኩ ተከብሮ እንዲያልፍ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ከሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች ጋር ውይይት አካሄዷል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት የፀጥታ ስራ የመንግስት ተልዕኮ ቢሆንም በዘላቂነት ማረጋገጥና የሀገርን ልማትና ዕድገት ማስቀጠል የሚቻለው በህዝቦች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ሲኖር መሆኑን ገልፀው በዚህም የወጣቶች ሚና የጎላ መሆኑን አብራርተዋል።
ወ/ሮ ሊዲያ አክለውም የዘንድሮ የኢሬቻ በአልን ሲከበር የጋራ ትርክትን በማስጠበቅ ፣ የሀገርንና የህዝቦችን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ እንዲሁም በአሉን ለማክበር ወደ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶችን ፍፁም በኢትዮጲያዊ ጨዋነት በመቀበል እሴትን በሚያጎለብት መልኩ ተከብሮ እንዲናያልፍ ወጣቶች ከወትሮው በበለጠ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን በመሆን የሚያጋጥሙ ችግርችን ጥቆማ በመስጠት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ በበኩላቸው ባለፍት ዓመታት በከተማው ላይ የተከበሩ የአደባባይ በዓላትና በርካታ ሁነቶች ፍጹም ሰላማዊ ሆነው እንዲያልፍ ወጣቶች ላደረጉት አስተዋዕኦ ምስጋናን አቅርበው መጭው የኢሬቻ በዓልም እንዳሁን ቀደሙ ፍጹም ሰላም ሆኖ እንዲያልፍ ወጣቱ የበኩሉን ሀላፊነት በመወጣት የጠላትን ሀይሎች ሴራ ሀሳባቸው እንዳይሳካላቸው በጋራ በመግባባትና በመተጋገዝ እንዳሁን ቀደሙ በዓሉን በሰላም ማክበር ይገባል ብለዋል።
አቶ ወቢ ጥላሁን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ በመድረኩ ተገኝተዋል እንዳሉት ወጣቱ ሀገርን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለበት የሚያምንና ግዴታውን የሚወጣ መሆኑን ጠቁመው እሬቻ ከአንድ ማህበረሰብ ባህላዊ ስርአት ባሻገር፣ የልዩነትን መከባበርና በጋራ መቆምን የሚጠናከር ፣ ለሀገራዊ አንድነት የሚያበረክቱ እሴቶች አስጠብቆ ማስቀጠል ይገባዋል ብለዋል።
የዘንድሮው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በአል በደመቀ መልኩ እንዲከበር የፀጥታና የደህንነት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።
መስከረም 19/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79