የአካባቢን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅና የከተማን ደህንነት ለማስቀጠል ለጥምር የፀጥታ መዋቅር የምሽት የፀጥታ ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የአካባቢን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅና የከተማን ደህንነት ለማስቀጠል ለጥምር የፀጥታ መዋቅር የምሽት የፀጥታ ስምሪት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም በማስጠበቅ የህዝቡን በሰላም ወጥቶ መግባት እያረጋገጠ ይገኛል።
ቢሮው በመጭዎቹ ቀናት የሚከበሩ የአደባባይ በአላት ሀይማኖታዊ እሴቱንና ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ተከብረው እንዲያልፉ አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በዚህም ዛሬ የከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ለጥምር የፀጥታ መዋቅሩ የምሽት ስማሪት ሰጥቷል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ የሀገርን ብሎም የከተማን ሰላም ለማደፍረስ የሚሞክሩ ግለሰቦችና ቡድኖችን ሴራ በማክሸፍ ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማና ህዝቦቿ በሰላም ወጥተው መግባት እንዲችሉ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም ይህን የተቀናጀ የፀጥታ ስምሪት በቀጣዩቹ ቀናት የሚከበሩ የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በአላት ያለምንም የፀጥታ ስጋት ተከብረው እንዲያልፉ ትልቅ አቅም መሆኑን ገልፀው የፀጥታ ሀይሉ በንቃት አካባቢን መጠበቅና የከተማን ሰላም በዘላቂነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ የዘንድሮው የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በአላት ለየት የሚያደርጋቸው ሀገራችን በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተከናወነውን ምርጫ መሰረት በማድረግ የመንግስት ምስረታ የሚካሄድበት እንደመሆኑ የፀጥታና የደህንነት ሁኔታን በልዩ ትኩረት መከታተልና መጠበቅ እንደሚገባ ገልፀው መጭዎቹ የአደባባይ በአላት ያለፀጥታ ችግር ተከብረው እንዲያልፉ በንቃት መጠበቅ ፣ የደንብ ጥሰቶችን መከላከል እንደሚገባ ገልፀዋል።
ወ/ሮ እቴማር የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት እንዳሉት ክ/ከተማዋ በርካታ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድበት እንደመሆኑ ያለፀጥታ ስጋት ነዋሪው ያለስጋት እንዲንቀሳቀስ ጥምር የፀጥታ ሀይሉ በሚወስደው ስምሪት መሰረት እያደረገ ያለው የቅንጅት ስራ ውጤታማ አድርጓል ብለው ይህንንም በቀጣይ ቀናት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
መስከረም 13/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79