በዓላት በሰላም እንዲከበር ቢሮው የሰላም ሰራዊቱ ከመላው ማህበረሰብና ከጸጥታው መዋቅር ጋር በመቀናጀት በቂ ዝግጅት አድርጓል።
በዓላት በሰላም እንዲከበር ቢሮው የሰላም ሰራዊቱ ከመላው ማህበረሰብና ከጸጥታው መዋቅር ጋር በመቀናጀት በቂ ዝግጅት አድርጓል።
አቶ ፍስሐ ጥበቡ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ
በኢትዮጲያ ከሚከበሩ የአደባባይ በአላት መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚገለፁ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአላት ሲሆኑ በአላቱ የህዝብ ለህዝብ ትስስር ና አንድነትን የሚያጠናክሩ የሀገርን ገፀታ የሚያንፀባርቁ ሀይማኖታዊና ህዝባዊ የምስጋና በአላቶች ናቸው ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ "ከተማችንን በአንድነት እንጠብቅ፤በዓላቱን በሰላም እናክብር" በሚል መሪ ቃል በከተማው ከሚገኙ የሰላም ሰራዊት አባላቶች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በአላቱ በከተማችን አዲስ አበባ በተያዘው ወር በድምቀት ሀይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱን ጠብቁ እንዲከበር የሰላም ሰራዊቱ ከፀጥታ ጥምር ሀይሉ ጋር በመሆን በሚሰጠው ስምሪት የአካባቢንና የከተማን ሰላም በማሰጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የውይይት መድረኩን ሲያስጀምሩ እንዳሉት የሰላም ሰራዊቶች የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ወስደው የአካባቢንና የከተማን ሰላም በማሰጠበቅ እየሰሩ ላለው ስራ ምሰጋና አቅርበው አልፍ አልፎ የኢትዮጲያን ገፅታ ለማጠልሸት የሚሰሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ሴራ በማክሸፍ በከተማችን የሚከበሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ የአደባባይ ሀይማኖታዊና ህዝባዊ በአላት ያለምን ፀጥታ ስጋት ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ እንዲያልፍ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በዓላቱ በአለም አቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስ የተመዘገቡ የሀገርን ገፅታ ለዓለም የምናሳይበት እንደመሆኑ ሀይማኖታዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው በአንድነትና በወንድማማችነት እንዲከበሩ በማድረግ ብሎም የመንግስት ምስረታ የሚካሄድበት በመሆኑ ጥንቃቄ በተሞላው መንገድ እንዲከበር በማድረግ በኩል በቂ ዝግጅት መደረጉን ሀላፊው አብራርተዋል።
ኮማንደር ጉማታው ገዳሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ በበኩላቸው በከተማው የሚታየው ሰላም ከህዝብ ጋር በተሰሩ ስራዎች መሆኑን ጠቁመው ለውጡን በማስቀጠል ገጽታው በሚያጎላ መልኩ በዓላቱ ተከብረው እንዲያልፉ ከተለያዩ የአለም ሀገራትና አካባቢዎች የሚመጡ ግለሰቦችን ደህንነታቸው በማስጠበቅ በዓላቱ በሰላም እንዲከበሩ የጸጥታ አካሉ ከመላው ማህበረሰቡ ጋር በጋራ በመሆን ሀላፊነታችሁን እንዲወጡ አሳስበዋል።
ኮማንደር ሙልጌታ በጋሻው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክተር ሲሆኑ በዓላት የማህበረሰብ የደስታ፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብና የመገናኘት ወቅቶች እንደመሆናቸው በዓላቶች በሰላም እንዲከበሩ የመንግሥት ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም የከተማው ነዋሪዎች፣ ወጣቶች፣ ማህበራት፣ የእምነት ተቋማት፣ ነጋዴዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የጋራ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አብራርተዋል።
የሰላም ሰራዊቶቹ በበኩላቸው በበዓላት ወቅቶ ብቻ ሳይሆን ሁል ጊዜም ሌት ተቀን እየሰሩ እንደሆነና በአሁኑ ወቅት ደግሞ የበለጠ በትኩረት እየሰሩ መሆናቸውን በመግለፅ በዓላቱ ከምንጊዜውም በላይ ፍጹም ሰላም እንዲሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።
መስከረም 13/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን