የጋራ የፀጥታ ስምሪት ሰላሟ ለተረጋገጠባት ከተማ !
የጋራ የፀጥታ ስምሪት ሰላሟ ለተረጋገጠባት ከተማ !
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ መጭዎቹ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአላት ሀይማኖታዊ ስርአቱንና ባህላዊ አሴቱን በጠበቀ መልኩ ተከብረው እንዲያልፍ በትኩረት እየተሰራ ሲሆን ዛሬም በአራዳ ፣ በጉለሌና በለሚኩራ ክ/ከተሞች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት የምሽት የፀጥታ ስምሪት ለጥምር የፀጥታ ሀይሉ ተሰጥቷል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አካባቢን ተቀናጅቶ መጠበቅ የከተማን ሰላም ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለው የምሽት ስምሪት መስጠት የከተማን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም መሆኑን ተናግረዋል። ኃላፊው አክለውም ሀገራችን የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል የፀጥታ ስምሪቱን አጠናክሮ የሚቀጥል እንደሆነና በቀጣይ የሚከበሩ የመስቀል ደመራ ፣ ኢሬቻና የመንግስት ምስረታ ያለፀጥታ ችግር እንዲያልፉ የመረጃ ልውውጥ ስርአትን ማዘመንና አካባቢን በንቃት መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ እንዳሉት የመስቀልና የኢሬቻ በአላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበሩና ህዝባችን በሰላም ወጥቶ መግባት እንዲችል ብሎም የሀገርን ሁለንተናዊ የዕድገት ጉዞና ለውጥ ለአለም ለማሳየት የፀጥታ መዋቅሩ ያለበት ድርብ ኃላፊነት በመረዳት ግዴታውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
አቶ አብዲ ሙሉነህ የአራዳ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ በስምሪቱ ላይ እንዳሉት ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ የከተማን ልማት በማስቀጠል ለህዝባችን በሰላም ወጥቶ መግባት ለማረጋገጥ የምሽት ስምሪት እየወሰዱ የአካባቢን ሰላም የሚያረጋግጡ ጥምር የፀጥታ ሀይሉ ምስጋናን ችረው የህዝብ አለኝታኘነቱን በማስቀጠል በቀጣይ ቀናት ለሚከበሩ በአላት ያለፀጥታ ስጋት ተከብረው እንዲያልፉ ማድረግ ላይ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
የአካባቢን ሰላም በማስጠበቅ የከተማን ሰላም ማረጋገጥ መቻሉ በስምሪቱ ወቅት የተገለፀ ሲሆን የሰላም ሰራዊት የሰላም አምባሳደር በመሆን የሚያደርጉትን የአከባቢን መጠበቅና ከመደበኛው የፀጥታ መዋቅር ጋር በቅንጅት መስራትን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል።
መስከረም 12/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79