በተያዘው በጀት ዓመት ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የተሻለ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት ይገባል ።
በተያዘው በጀት ዓመት ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የተሻለ አገልግሎት ለህብረተሰቡ መስጠት ይገባል ።
አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ላይ የሰላም የጸጥታና የደህንነት ስራዎችን ከመስራት ጎን ለጎን አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በጊዜው በመፍታት ችግሮች እንዳይከሰቱ እየሰራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዛሬው ዕለት በአገልግሎት አሰጣጥና ላይ ከተገልጋይ መማክርት ምክር ቤት አባላት ጋር ምክክር አድርጓል።
በምክክር መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ዋና አማካሪ ሲሆኑ ቢሮው ባለፈው በጀት ዓመት ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በአገርና በከተማ ደረጃ ትላልቅ ድሎች ታስበው የተሳኩበትና የተጠናቀቁበት ስኬታማ አመት መሆኑን አስታውሰው
በተያዘው በጀት ዓመት ሀገራችን ካለችበት ስኬት መነሻ በማድረግ በበለጠ ተግቶ በመስራት በሚገባው ልክ የጋራ መግባባት የተፈጠረበት አዲስ የመንግስት ምስረታ የሚመሰረትበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ቢሮው ህዝቡን ያሳተፈ የሰላም የጸጥታና የደህንነት ስራዎችን የመስራቱ ኢደቱ እጅግ የጠነከረ ነውም ያሉት አማካሪው የአገልግሎት አሰጣጥ ኢደቱ የጠነከረም ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከህብረተሰቡ የሚመጡ ሀሳቦች ለቢሮው ትልቅ አቅምን በመፍጠርና በመፈተሽ የተጀመሩ ስራዎችን በቀጣይ በቴክኖሎጂ በመጠቀም የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን የተሻለ ስራ መስራትም ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።
ወ/ሮ አለም ጸሀይ ማሞ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥና ስታንዳርዳይዜሽን ዳይሬክተር እንዲሁም በአቶ በላይ ጥላሁን የተገልጋይ መማክርት የምክር ቤቱ አባል አማካኝነት ለመወያያ የሚሆን መነሻ ጹሁፍ ያቀረቡ ሲሆን የአገልግሎት አሰጣጥ ተቋሙ ለተገልጋዮች የሚሰጠውን አገልግሎት በግልጽነት፣ በተጠያቂነት፣ በፍትሐዊነት፣ በፍጥነትና በተገልጋይ እርካታ ላይ በመመስረት ለማሻሻል እንደሚገባ አብራርተው
በዚህ መሠረት የተገልጋይ መማክርት ጉባኤ በማዘጋጀት የተገልጋዮችን አስተያየት፣ ቅሬታ፣ ጥያቄና ምክረ-ሐሳብ በመሰብሰብ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እንደሚጠቅም ገልፀዋል።
ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው በጋራ የሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ በመወያየት ለሀገር ሰላምና ብልጽግና በመቆም እንዲሁም የሚገጥሙ ችግሮች የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሆነው ወደ ግጭት እንዳይኔዱ በህብረት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
መስከረም 12/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79