የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ ፉፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የሀይማኖት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ።
የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ ፉፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የሀይማኖት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ።
መስከረም 11/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የሃይማኖት አባቶች የደመራ አስተባባሪዎችና የሰንበት ተማሪዎች ሚናና ኃላፊነት ዙሪያ ውይይት ተካሔዷል።
ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ዋና አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ እንደተናገሩት ከፊታችን የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበር አባቶችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ድርሻ የጎላ በመሆኑ በአብሮነትና በወንድማማችነት ማክበር እንደሚገባ ገልፀዋል።
አቶ አከበረኝ ወጋገን የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ በበኩላቸው የመስቀል ደመራ በዓል ከሀገር አልፎ የአለም ህዝብ ቅርስ በመሆኑ በዓሉን ለመታደም የሚመጡ ታዳሚያን ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ይከበር ዘንድ የሃይማኖት አባቶች፣ የደመራ አስተባባሪዎችና የሰንበት ተማሪዎች ሚናና ተሳትፎ ወሳኝ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ሀይሉ በበኩላቸው ከፊታችን የሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በፍፁም ሰላም የሃይማኖት ስርዓቱ በሚያዘው መልኩ ተከብሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ የሃይማኖት አባቶችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸው ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ሀላፊ ኮሚሽነር ሞቱማ ሲማ በበኩላቸው የመስቀል ደመራ በዓል በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር ከሀይማኖት አባቶች እና ከሚመለከታቸው አካላት በትብብርና በቅርበት ይሰራል ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የመስቀል ደመራ በዓል ሀይማኖታዊ ስርዓቱንና እሴቱን ጠብቆ ይከበር ዘንድ የድርሻቸው እንደሚወጡ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።
See less