ሰላሟ ለተረጋገጠባት ከተማ የምሽት ጥምር የፀጥታ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ሰላሟ ለተረጋገጠባት ከተማ የምሽት ጥምር የፀጥታ ስምሪት መስጠትና ለጋራ ዓላማ መቆም ወሳኝ ነው።

ሰላሟ ለተረጋገጠባት ከተማ የምሽት ጥምር የፀጥታ ስምሪት መስጠትና ለጋራ ዓላማ መቆም ወሳኝ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በመስከረም ወር የሚከበሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ የአደባባይ በአላት ያለ ፀጥታ ችግር እሴታቸውን ጠብቀው ተከብረው እንዲያልፉ ለአዲስ ከተማና ለጉለሌ ክ/ከተሞች ጥምር የፀጥታ ሀይል ከሸገር ከተማ የፀጥታ ሀይል ጋር የምሽት የፀጥታ ስምሪት ሰጥቷል።

አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት በከተማችን የሚከበሩ በአላት ሀይማኖታዊ ስርአታቸውንና ባህላዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው እንዲያልፉ የፀጥታ ጥምር ሀይሉ በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ በቀኩላቸው ከፊታችን የሚከበሩ በአላት የአደባባይ በአላት እንደመሆናቸውና በአሉን ለማክበር ወደ ከተማዋ የሚገቡ እንግዶችን በኢትዮጲያዊ ጨዋነት መቀበል እንደሚያስፈልግ ገልፀው በተለይም የደንብ ጥሰቶች እንዳይኖሩ ተናቦ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ለጥምር የፀጥታ ሀይሉ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቁና የማያጋጥሙ የፀጥታ ስጋቶች ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ የከተማውን ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባ ስምራት ተሰጥቷል።

መስከረም 8/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79