የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር የበአሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ውይይት ተካሄደ።
የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር የበአሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ውይይት ተካሄደ።
በአሉ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ የጋራ ጥንቃቄ በመውሰድ በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱንና ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በሰላምና በአንድነት እንዲከበር ከክርስትና ሃይማኖት አባቶች የበአሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ውይይት አድርጓል።
ቢሮው በከተማዋ የሚካሄዱ የአደባባይ በአላት ያለምንም የፀጥታ ስጋት ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ አብሮነትን በማጠናከር እርስ በርስ የመከባበር ባህልን ባዳበረና የሀገርን መልካም ገፅታ በሚገነባ መልኩና ሀይማኖታዊ አስተምሮውን በጠበቀ መልኩ ሆኖ እንዲያልፍ ከሀይማኖት አባቶችና ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር እየሰራ ይገኛል።
አቶ ተስፍዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት በዓሉ በአለም አቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስ የተመዘገበና ሰፊ ህዝብ የሚሳተፍበት በመሆኑ፣ የህዝብ ደህንነትን ማረጋገጥ፣ የሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቱን በማክበርና ሰላማዊ የበዓል ድባብን መጠበቅ የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ የሃይማኖት አባቶች ፣ የፀጥታ አካላትና ህብረተሰቡ በቅንጅት በአሉ በሰላምና በመከባበር ለማክበር የሚያስችል የጋራ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባና የሀይማኖት አባቶችም ምዕመኑን ማስገንዘብ እንደሚገባቸው ገልፀዋል።
በውይይቱ ወቅትም በበአሉ አከባበር ወቅት የሚደረጉ ጥንቃቄዎችና አጠቃላይ ዝግጅትን በተመለከተ ሰፊ ውይይት አካሄደው የጋራ አቅጣጫ ወስደዋል ።
መስከረም 8/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79