በቀጣይ ቀናት የሚከበሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በቀጣይ ቀናት የሚከበሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራን በሚመለከት ከፀጥታ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

በቀጣይ ቀናት የሚከበሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራን በሚመለከት ከፀጥታ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ።

መስከረም 08/2019 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመጪው ቀናት የሚከበሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ሐይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴታቸውን በጠበቀ መልኩ ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ የሚያስችል ውይይት ከፀጥታ አካላት ጋር አካሔዷል።

አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ዋና አማካሪ በቀጣይ ቀናት የሚከበሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ የአደባባይ በዓላት በተሳካ ሁኔታ በፍፁም ሰላም ለማክበር የፀጥታ አካላት ሚና መናበብና ቅንጅት እንዲሁም ስምሪት ወሳኝ ነው ሲሉ ተናግረው የከተማችንን ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም የፀረ ሰላም ሀይሎችን ሴራና እንቅስቃሴ በንቃት መረዳት ተገቢ ነው ብለዋል።

አቶ ሙሉቀን ዮሀንስ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽህፈት ኃላፊ በበኩላቸው ሁለቱም የአደባባይ በዓላት በርካታ ህዝብ የሚታደምባቸው እንደመሆናቸውና ከኢትዮጲያ አልፈው የአለምን ትኩረት የሳቡ በመሆናቸው በቅንጅትና በተናበበ የፀጥታ ስምሪት ሀይማኖታዊ ስርዓቱንና ባህላዊ ትውፊትን ባስጠበቀ መንገድ ለማክበር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የፀጥታ ጥምር ግብረ ሃይል አባላት በበኩላቸው ሁለቱም ታላላቅ በዓላት ሀይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊታቸውን በጠበቀ መልኩ እና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚፈጥሩትን አዎንታዊ ተፅእኖና ገፅታ ግንባታ በሚያረጋግጥ መልኩ ተከብረው እንዲያልፉ በየደረጃው ያሉ የፀጥታ አካላት የእለት ተዕለት ስራ ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ለውጤታማነቱ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በቀጣይ ቀናትም የፀጥታና የደህንነት ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ተመላክቷል።

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79