መስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት በሰላም፣ በፍቅርና...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

መስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት በሰላም፣ በፍቅርና በመቻቻል እንዲከበሩ የፀጥታ መዋቅሩ የቅድመ ጥንቃቄና የጸጥታ ዝግጅቱን አጠናክሯል።

መስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት በሰላም፣ በፍቅርና በመቻቻል እንዲከበሩ የፀጥታ መዋቅሩ የቅድመ ጥንቃቄና የጸጥታ ዝግጅቱን አጠናክሯል።

በኢትዮጲያውያኖች ዘንድ በልዩ ድምቀትና ብዙ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ አደባባይ ወጥቶ የሚያከብራቸው በአላቶች በተያዘው መስከረም ወር የሚከበሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአላት ሲሆኑ በአላቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብረው እንዲያልፉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽንና የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ከመአከል እስከ ወረዳ ካሉ ሰራተኞች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን ከፀጥታ አካሉ ጋር በመቀናጀት በመናበብ እየተሰራ የሚገኘውን የፀጥታና የደህንነት ስራን በቀጣይ ቀናትን አስቻይ ስልቶችን በመቀየስ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት በአላቱ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶችን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ እንዲያልፍ በልዩ ትኩረት ህብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በቀሪዎቹ ቀናትም በበአላቱ አከባበር ላይ የተከለከሉ ጉዳዮችን ለህብረተሰቡ ማሳወቅ ፣ የፀጥታ መዋቅሩ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በቅንጅት የቅድመ ጥንቃቄና በተለይም ፀጉረ ልውጦችን መከታተል ፣ የፀጥታ ስጋት ቦታዎችን መለየትና አፋጣኝ መፍትሄ መወሰድ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ወንድማገኝ ታደሰ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ኃላፊ እንደገለፁት በዓላቱ በርካታ ህዝብን ወደ አደባባይ በመውጣት የሚያሳትፍበትና ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ከተማችን የሚገቡበት እንደመሆኑ የታዳሚዎችን ደህንነት፣ የእንቅስቃሴ ምቹነትና የሰላማዊ አከባበር ሁኔታን ለማረጋገጥ የፀጥታ መዋቅሩ በቅንጅት እየሰራ ያለውን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ህብረተሰቡም የፀጥታ ስጋት ከሚፈጥሩ ድርጊቶችን በመቆጠብ፣ ህግን በማክበር፣ ለፀጥታ አካላት በመተባበርና አጠራጣሪ ሁኔታዎችን በአግባቡ በማሳወቅ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ የፀጥታ መዋቅሩ ለህዝቡ በማሳወቅ በቅርበት መስራትና ትኩረት መስጠት እንደሚጠበቅ ኃላፊው አሳስበዋል።

በሁለቱም ዘርፍ የፀጥታ ስጋት የሚሆኑ ገዳዮችንና ቦታዎችን የመለየት ፣ የሚያጋጥሙ የፀጥታ መደፍረሶችን መከላከልና አስፈላጊውን እርምጃና ጥንቃቄ መውሰድ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

መስከረም 8/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c7