የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ የፀጥታ ጥምር ሀይሉ በየአካባቢው በተጠናከረ የምሽት ስምሪት ላይ ይገኛል።
የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ የፀጥታ ጥምር ሀይሉ በየአካባቢው በተጠናከረ የምሽት ስምሪት ላይ ይገኛል።
በቅንጅት፣ በንቃትና በቁርጠኝነት የሚከናወነው የምሽት ስምሪት የህዝቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማስጠበቅና ለፀጥታ መደፍረስ ቦታ ላለመስጠት በንቃትና በመናበብ የከተማን ሰላም ለማረጋገጥ ወሳኝ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በየካ ክ/ከተማ ለፀጥታ ጥምር ሀይሉ የምሽት የፀጥታ ስምሪት ሰጥቷል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት ለሰላም ዘብ መቆም የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት እንደመሆኑ የፀጥታ ጥምር ሀይሉ የሀገራችን ጠላቶችን በማንበርከክ የሀገራችንን ብሎም የከተማችንን ሰላም በማረጋገጥ የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ ዕውን ለማድረግ በቁርጠኝነት በመረባረብ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
በተያዘው ወር የሚከበሩ የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በአላት በአለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ በማይዳሰስ ቅርስ የተመዘገቡ የኢትዮጲያን ከፍታ የሚያረጋገጥና ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴትን በጠብቁ በሆነ መልኩ ተከብረው እንዲያልፉ የፀጥታ ጥምር ሀይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ አቶ ተስፋዬ አሳስበዋል።
አቶ እንዳልካቸው የየካ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የመስቀልና የኢሬቻ በአላት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበሩ የጋራ ስምሪት መሰጠቱ ሰላምን ለማደፍረስ የሚተጉ ሀይሎችን ዕቅድ በማክሸፍ የኢትዮጲያን ከፍታ ለማረጋገጥ አጋዥ መሆኑን ገልፀው ጥምር ሀይሉ በንቃት በመጠበቅ በአላቱ በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
የምሽት የፀጥታ ስምሪቱ ለአዲስ አበባ ጥምር የፀጥታ ግብረሀይልና ለሸገር ከተማ የፀጥታ ግብረሀይል በጋራ የተሰጠ ሲሆን ሁለቱ ከተሞች በቅንጅት የሚሰሩትን የፀጥታና የደህንነት ስራዎችን የሚያጠናክር መሆኑ በስምሪቱ ላይ ተመላክቷል።
መስከረም 7/2019 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!
የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79