"በማህበረሰብ መካከል ውይይቶችን ማመቻቸት፤ መግ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

"በማህበረሰብ መካከል ውይይቶችን ማመቻቸት፤ መግባባትን መገንባትና ሰላምን ማፅናት ወሳኝ ነው። "

"በማህበረሰብ መካከል ውይይቶችን ማመቻቸት፤ መግባባትን መገንባትና ሰላምን ማፅናት ወሳኝ ነው። "

አቶ ፍስሀ ጥበቡ

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

በአዲስ አበባ ከተማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሶስት ክፍለ ከተሞች የተሳተፉበት የማህበረሰብ ተኮር ምክክር ግንዛቤ እንዲሁም የመስቀልና የኢሬቻ በአል አከባበር ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደደር ቢሮ የተዘጋጀው ይህ መድረክ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማን ጨምሮ ኮልፌ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች የተሳተፉበት ሲሆን በእለቱ የከተማና የክፍለ ከተማ አመራሮች ከ3ቱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የብሎክ አመቻቾች፣የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።

በእለቱ የማህበረሰብ ተኮር ምክክር አስመልክቶ የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን በሰነዱ ላይ የተግባቦት አይነቶች የአመቻቾች ሚና እንዲሁም በምክክሩ የተገኙ ውጤቶችና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አስመልክቶ ከተሳታፊዎች ጋር የጋራ ግንዛቤና ተግባቦት ተፈጥሯል።

በእለቱ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍሰሀ ጥበቡ ባለፉት 46 ቀናት ከ4ሺ በላይ ከተለያዩ የኢትዮጲያ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎች የተሳተፉበት ሀገራዊ ምክክር በማካሄድ አሻጋሪ የሆኑ ሀሳቦችን እንዲሁም አለመግባባቶችን በውይይት መፍታት እንደሚቻል ያሳየ ውይይት መካሄዱን ገልጸዋል።

አክለውም ምክክር ኮሚሽኑ ሀገራችንን አንድ እርምጃ በማሻገር የውይይት ባህል የሚያዳብር መሆኑንን ገልፀው የተዘጋጀው መድረክም ልዩነትን ወደ ውይይት ውይይትን ወደ መግባባት መግባባትን ደግሞ ወደ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ደረጄ ድሪብሳ በበኩላቸው

በክፍለ ከተማው የወንጀል ምጣኔ በ56% መቀነሰ የተቻለ መሆኑን ገልፀው ለዚህም ህብረተሰቡን ያሳተፉ ውይይቶች ለዘላቂ ሰላም መፍትሄ መሆናቸውን ጠቁመው መጪው የመስቀልና የኢሬቻ በአል በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

መስከረም 7/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79