የጋራ መግባባትና ስምምነት ለዘላቂ ሰላም"

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የጋራ መግባባትና ስምምነት ለዘላቂ ሰላም"

የጋራ መግባባትና ስምምነት ለዘላቂ ሰላም"

ከብሎክ እስከ ክ/ከተማ ሲካሄድ የቆየው የወጣቶች ውይይት በከተማ አቀፍ ደረጃ የማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ላይ ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት ህዝብን ያሳተፈ የጸጥታ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን "የጋራ መግባባትና ስምምነት ለዘላቂ ሰላም " በሚል መሪ ቃል ከተማ አቀፍ የወጣቶች ኮንፈረንስ የማጠቃለያ መርሐ ግብር አካሂዷል።

አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ተወካይና የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ሀላፊ በኮንፈረንሱ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በሰላም ጉዳይ ላይ የወጣቱ ሚና አይተኬ መሆኑን ገልፀው ሀገራችን ኢትዮጵያ ብዙ የጠላት ሀይሎች ቢመኙአትም ወጣቶች በተቀናጀ መልኩ በመሆን የጠላትን ሴራ ማክሸፍ ተችሏል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም በመጪዎቹ ቀናት የሚከበሩት የአደባባይ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ገልፀው በዓላቱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶችን ጠብቀው እንዲከበሩ ወጣቶች የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ ብዙ ባህላዊ ቅርሶችና የተለያዩ ማንነቶች ያሏት ሀገር እንደሆነች ጠቅሰው እነዚህ ብዝሃ ሀብቶች በትብብር ከተጠቀሙባቸው ለዕድገት ጠንካራ መሠረት እንደሆኑ አመልክተዋል።

አቶ ዳዊት ትርፉ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ ተወካይ በበኩላቸው በየአካባቢው በርካታ ውይይቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስታውሰው ወጣቱ የሰላም ምንነት የገባው ዘመናዊ ባህሪን የተላበሰ ለከተማ ሰላም የማይተኛ መሆኑን ባለፉት ጊዚያት ባለፉ ሀገራዊና ከተማአቀፋዊ ሁነቶች ያለፀጥታ ችግር ማለፍ መቻላቸው ምስክር ናቸው ብለው ከፊታችን የሚከበሩ በአላት በሰላም እንዲያልፉ ወጣቱ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን በቅንጅት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ በበኩላቸው ወጣቶች የሀገር ኃይልና የወደፊት ተስፋ እንደመሆናቸው ባላቸው አቅምና በፈጠራ ችሎታቸው ለሀገር ልማትና ለሰላም ግንባታ አበርክቷቸውን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

ሀገር እንድትፀናና ሰላሟ እንዲረጋገጥ የወጣቶች ሚና የጎላ ነው ያሉት አቶ ክብረአለም ደምሴ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሲሆኑ በቀጣይ ቀናት የሚከበሩ በአላት ሰላማዊ ሁነው እንዲከበሩ በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።

መስከረም 7/2019 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79