"በመጪው ቀናት የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት ፍፁ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

"በመጪው ቀናት የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብረው እንዲያልፉ የአንድ መአከል የፀጥታ ስምሪት ተሰጠ።"

"በመጪው ቀናት የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብረው እንዲያልፉ የአንድ መአከል የፀጥታ ስምሪት ተሰጠ።"

መስከረም 06/2019 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፣ 03 እና 11 አስተዳደሮች ከአጓራባች ሸገር ሲቲ ፉሪ ክፍለ ከተማ ጋር በመቀናጀት የአንድ መአከል የፀጥታ ስምሪት ተሰጥቷል።

በስምሪቱም የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ ደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች፣ የቅጥር ጥበቆች ፣ የሸገር ሚሊሻዎች ፣ ራያ ነጌኛ እና የሰላም ሰራዊት አባላት ተሳትፈዋል።

በመርሀ ግብሩ በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ምክትል ቢሮ አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ ፤ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት የህዝብ የአደባባይ እሴቶች እንደመሆናቸው በአንድነት፣ በፍቅር እንዲሁም ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ባጠናከረ መልኩ ሊከበሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ህብረተሰቡም በዓላቱን ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ የጨዋነትና የእንግዳ ተቀባይነት ባህል በመቀበል እንዲሁም ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በቅንጅት በመስራት፣ በዓላቱ በደመቀና ባማረ ሁኔታ እንዲጠናቀቁ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

​የክፍለ ከተማው የሰላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ኃይሉ በበኩላቸው፤ በክፍለ ከተማው የሚገኙ ሁሉም የፀጥታ መዋቅሮችና የሰላም ሰራዊት አባላት ከአጎራባች የሸገር ከተማ ክፍለ ከተሞች ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀው፣ እየተከናወኑ ያሉ የደህንነት ስራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ይህ የጋራ ቅንጅት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል።

የወረዳ 11 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀጋዬ ኩማ በበኩላቸው እስካሁን ለተከናወኑ የሰላምና ፀጥታ ስራዎች ምስጋና አቅርበው፤ በቀጣይም የሰላም ሰራዊቱ ከፀጥታ ኃይሎች፣ ከደንብ ማስከበር ኦፊሰሮችና ከአመራሩ ጋር ይበልጥ ተቀናጅቶ በመስራት በዓላቱ ፍጹም ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የስምሪቱ ተሳታፊዎች የተሰጣቸውን ሀገራዊና ህዝባዊ ኃላፊነት በቁርጠኝነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ሰላም ከሁሉም... በሁሉም... ለሁሉም!

የፀጥታ መረጃ ጥቆማ ለመስጠት፦ 8882 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79